ሲዳማ ቡና የኮከባቸውን ውል አራዘሙ !
በዛሬው እለት በንቃት ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው ለመቀላቀል እየተስማሙ ያሉት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ላይ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቻቸውን ውል ማራዘማቸው ተሰምቷል ።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት የሲዳማ ቡና ድንቅ እንቅስቃሴ ምንጭ የሆነው ዳዊት ተፈራ ( ኦዚል ) በሲዳማ ቤት ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል ።
ዳዊት ተፈራ በተለይም በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ በርካታ የሊጉ ክለቦች አይናቸውን ቢያሳርፉበትም ምርጫውን ሲዳማ ቡና አድርጓል ።