ሲዳማ ቡና የተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘሙ ተጠምደዋል !
በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ጎልተው መውጣት ከቻሉ መካከል አንዱ የሆነው አበባየሁ ዮሐንስ በሲዳማ ቤት ውሉን ማራዘም ችሏል ።
አበባየሁ ዮሐንስ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከአዲስ ግደይ እና ከሀብታሙ ገዛኸኝ ጋር የነበራቸው ጥምረት በሊጉ ሌላ ድምቀት ሲሆን በሊጉ ሲዳማ ቡና በርካታ ጎሎችን በተጋጣሚው ላይ ሲያሳርፍ የራሱን አስተዋፅዖ ማበርከት ችሏል ።
ሲዳማ ቡና በዛሬው ዕለት በይፋ የግብ ጠባቂውን ፍቅሩ ወዴሳን ጨምሮ በሊጉ ክለቦች በጥብቅ ሲፈለግ የቆየውን የመስመር ተጫዋች ዮናታን ፍሰሐ ውል በይፋ አራዝመዋል ።