ሲዳማ ቡና የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

 

የተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በሊጉ ልምድ አላቸው ከሚባሉ የውጭ ሀገር የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች አንዱ የሆነውን የሰንደይ ሙቱኩን ኮንትራት አራዝሟል ።

ኬንያዊው የመሐል ተከላካይ ለቀጣይ ሁለት ዓመት በሲዳማ ቡና ቤት የሚያቆየውን ውል ከጥቂት ሰዓታት በፊት መፈራረሙ ይፋ ሆኗል ።

ሀትሪክ ስፖርት ከተጫዋቹ ጋር ከፊርማ ስነ ስርዓቱ በኋላ ቆይታ ስታደርግ ” ሁለተኛ ቤቴ በሆነው ክለብ ሲዳማ ቡና ጋር ውሌን በማራዘሜ ደስተኛ ነኝ ። የአሰልጣኙን የአጨዋወት ዘይቤ ለመረዳት ችያለው በቀጣይ ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር በአፍሪካ የውድድር መድረኮች ላይ ተሳተፊ ለመሆን ጠንክሬ እሰራለሁ ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል ።

ሰንደይ ሙቱኩ ከሌሎች ክለቦች በተለይም በባህር ዳር ከተማ በጥብቅ ቢፈለግም በሲዳማ ቡና ቤት ውሉን አራዝሟል ::

ከሰንደይ ሙቱኩ በተጨማሪም ሲዳማ ቡናዎች የብርሀኑ አሻሞን ውል ማራዘም ሲችሉ በመጪው ቀናት የነባር ተጫዋቾችን ውል ጨምሮ አዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor