ሲዳማ ቡና አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል !

 

በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እየተመሩ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች ከኮከባቸው እና አምበላቸው አዲስ ግደይ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ የባህርዳር ከተማውን አጥቂ ማማዱ ሲዲቤን በምትኩ ማምጣታቸው ተሰምቷል ።

ማሊያዊው የፊት መስመር አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አንስቶ በሊጉ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ላይ ጥሩ ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ታይቷል ::

ማማዱ ሲዲቤ የጣና ሞገዶቹን ከመቀላቀሉ በፊት በጅማ አባ ጅፋር ተጫውቶ ማሳለፉ አይረሳም ።

ማማዱ ሲዲቤ ከመቐለ 70 እንደርታው የፊት መስመር አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በመቀጠል በሊጉ ከሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች ሁለተኛው ኮከብ ግብ አግቢ ነው ።

ሲዳማ ቡና ከማማዱ ሲዲቤ በተጨማሪም የአጥቂ መስመሪ ተጫዋች የሆነዉን ሀብታሙ ገዛኸኝ ዉል ለተጨማሪ ሁለት አመት ማራዘሙ ተገልጿል።

ሀብታሙ ገዛኸኝ በሲዳማ ቡና ድንቅ ብቃቱን እያሳዬ የክለቡ ወሳኝነቱን ባለፉት አመታት ያስመሰከረ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ አመታት ክለቡን የዋንጫ ተፎካካሪ ለማድረግ ተስማምቷል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor