ሰይድ ሀብታሙ ስለ ወቅታዊ አቋሙ እና እግር ኳስ ህይወቱ ይናገራል።

👉👉 ወደ ጅማ ስመጣ ለሶስተኛ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ ነበር

👉👉 ብሄራዊ ቡድን የሚጠብቅልህ ኢትዮጵያዊ ግብ ጠባቂ ነው እንጂ ከውጭ የሚመጡት አይደሉም

👉👉 የመጫወት እድሉ እያገኙ ያሉት የውጭ ግብ ጠባቂዎች ናቸው ስለዚህ ፌደሬሽኑንም ክለቦችም በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል

 

በሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ግባቸውን ለማስጠበቅ አይናፋርነት የያዛቸው ክለቦቻችን። የግል ጥረቱን ተጠቅሞ የውጭ ግብ ጠባቂን ተቀያሪ ወንበር ላይ ማስቀመጥ ችሏል የዛሬው እንግዳችን የጅማ አባጅፋሩ ግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ።

ስለ ትውልድ እና የእግር ኳስ አጀማመር ሂወትህ
ብንጀምር

እኔ የተወለድኩት ጅማ ነው። ያደኩት ደግሞ ወደ ኢሉባቡር መቱ ነው። እግር ኳስን የጀመርኩት ሰፈር ውስጥ በመጫወት ነው። በፕሮጀክትም በግብ ጠባቂነት እሰራ ስለነበር አሁን ላለሁበት ደረጃ ረድቶኛል። በክለብ ደረጃ መጀመሪያ ለመቱ ከታማ በመጫወት ነው የጀመርኩት። 2009 ላይ ደግሞ ወደ ከፋ ቡና በማምራት እስከ 2010 ቆይቸ። 2011 ደግሞ ለአርባምንጭ ከተማ መጫወት ችያለው። ከዛ 2012 ጥሩ እየተንቀሳቀስኩ ወዳለሁበት ጅማ አባጅፋር መቀላቀል ችያለው።

በዘንድሮ የውድድር አመት ድንቅ ብቃትህን እያሳየህ ነው እና ምትገኘው ሚስጥሩ ምንድነው?

ዋናው መታመን ነው። አንድን ተጫዋች ስታስገባው ልታምነው ይገባል። ግብ ጠባቂም ሆነ ሌሎች ክፍል ላይ ሚጫወት ተጫዋች ስታምነው ነው ጥሩ ሊንቀሳቀስልህ ሚችለው። አንደኛ ያው ፈጣሪን ከያዝክ ሁሌም ይሳካልሀል። ሁለተኛ አሰልጣኞቼ የሚሰጡኝን ስልጠና ጠንክሬ በመስራት ነው ለዚህ የበቃሁት። ወደ ጅማ ስመጣ ለሶስተኛ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ ነበር። ቢሆንም ባሳየሁት ጥሩ ብቃት ቀዳሚ ተሰላፊ መሆን ችያለው። የምለው ቢኖር ጠንክሮ መስራት ትልቅ ደረጃ ያደርሳል። ካልሰራህ ደግሞ የትም ልትደርስ አትችልም። በውጭ ግብ ጠባቂዎች ምክንያት ተቀያሪ ወንበር ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን ግብ ጠባቂዎች በዚህ አጋጣሚ ላስተላልፈው የምፈልገው ነገር ተስፋ ሳይቆርጡ፣፣ አንድ ቀን አለ ብለው ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ስራችን በጣም ትግል ይፈልጋል። በተሰጠን አጋጣሚ ጥሩ ለመንቀሳቀስ መሞከር ነው። የውጭ ግብ ጠባቂዎች ምንም የተለየ ነገር የላቸውም በአንድ ጨዋታ አራት እና አምስት ግቦች እየተቆጠሩባቸው ነው። እና እኛም ምንድነው ወደኋላ ያስቀረን ነገር ብለን ማሰብ መቻል አለብን። ጠንክረን መስራት ስንችል ነው የውጭ ግብ ጠባቂዎችን ማስቀረት ምንችለው።

በውጭ ጠባቂዎች ግባቸውን ለሚያስጠብቁ ክበለቦች ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት

ለክለቦች የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር። ኢትዮጵያዊያን ግብ ጠባቂዎች ብንጠቀም ውጮችን ባናይ ምክንያቱም አንድ የሀገር ልጅ ነው። ሁለተኛ ብሄራዊ ቡድን የሚጠብቅልህ ኢትዮጵያዊ ግብ ጠባቂ ነው እንጂ ከውጭ የሚመጡት አይደሉም። በተጨማሪም ኢኮኖሚያችንን እንቆጥባለን እናም የተሻለ ሚሆነው የራሳችን ተጫዋቾች ብናሳድግ ነው ምለው። ከፕሪምየር ሊግ አልፎ ከፍተኛ ሊግም የውጭ ግብ ጠባቂዎች አሉ ከታች ያሉት ተጫዋቾች እድል እያገኙ አይደለም ይን ነገር ደግሞ ፌደሬሽኑ ጠለቅ ብሎ ሊያስብበት ይገባል። ለምን ብትለኝ ብሄራዊ ቡድናችንም እየተጎዳ ያለው በግብ ጠባቂዎች እጦት ነው። ምክንያቱም ከተቀያሪ ተነስቶ ግብ ጠብቅ ብትለው ጥሩ ላይንቀሳቀስ ይችላል። የመጫወት እድሉ እያገኙ ያሉት የውጭ ግብ ጠባቂዎች ናቸው ስለዚህ ፌደሬሽኑንም ክለቡም በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል። ለምሳሌ ቻይናን ስናይ የሌላ ሀገር ግብ ጠባቂዎች ወደ ሀገሯ እንዳይጉቡ ከልክለዋል። እኛም ጋር ተመሳሳይ ነገር ቢኖር የተሻለ ነው።

በሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂ አምኖ እንድትሰለፍ ላረገህ ጅማ አባጅፋር ምን ትላለህ

በመጀመሪያ ክለቡ ውስጥ እንድካተት ስላደረጉኝ ከልብ ማመስገን እፈልጋለው። ሲቀጥል በኔ እምነት ኖሯቸው እንድሰለፍ ያደረጉኝ አሰልጣኞቼ ሳላመሰግን አላልፍም። እዚህ እንድደርስ ያገዙኝ የቡድን አጋሮቼንም አመሰግናለው።

በብሄራዊ ቡድን ስለመጫወት

አንድ ሰው በሚሰራው ስራ ላይ የሆነ ግብ አለው። ያን ግብ ደግሞ ለማሳካት ጠንክሮ መስራት አለበት። የአላህ ፍቃድ ከሆነ ደግሞ የሀገሬን ብሄራዊ ቡድንን ማገልገል ነው ዋናው አላማየ።

እዚህ እንድደርስ አስተዋፅኦ አላቸው የምትላቸውን እንድታመሰግን እድል ልስጥህ

በመጀመሪያ ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለን። ከዛ ቀጥሎ እዚህ እንድደርስ ያደረጉኝ ወላጆቼን እና አሰልጣኞቼን ማመስገን እፈልጋለው። ድሮ ስጫወት አይዞህ በርታ ትልቅ ደረጃ ትደርሳለህ እያሉ ሲያበረታትቱኝ ለነበሩ ሁሉ። ሀገሬን ለማገልገል ትልቅ አላማ እንዳለኝ በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለው።

የመጨረሻ ጥያቄን ላርገው እና እንግዲህ የፊታችን የካቲት 8 ቀን  ልታገባ ነው እና ያለውን ነገር አውራኝ

ሳቅ ሳቅ እንግዲህ የአላህ ፍቃድ ከሆነ ከምወዳት የፍቅር አጋሬ ሊና ናስር በ8 ሰርግ አለብን። ያው እንግዲል ሰርጋችን ያማረ ይሁን ነው እምለው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor