አዲስ አዳጊዎቹ ሰበታ ከተማዎች የሥስት የውጪ ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።
ውበቱ አባተ የአጥቂ መስመር ክፍላቸውን ለማጠናከር ቡሩኪናፋሲያዊውን ዲያዋራ ባኖን አስፈርመዋል።ከዚህ ቀደም ለቤልጅየሙ ክለብ ኤፍሲ ቱቢዜ፣ለሞሮኮው ፋር ራባት፣ለግብፁ ሶምሀ፣ለአልጀርያው ጄይኤስ ካቢሌይና ለሀገሩ ክለብ ቦቦ ዲዮላሶ መጫወት የቻለው የ27 ዓመቱ ዲያዋራ ሰበታዎችን መቀላቀል ችሏል።
ሁለተኛው ፈራሚ የመስመር አጥቂ ፈራሚ ሲላ አሊ ባድራ ሲባል ይህም በተመሳሳይ ቡሩኪኒያፋሳዊ ሲሆን ብሄራዊ ቡድኑንም ወክሎ መጫወት ችሏል።ሥስተኛው ፈራሚ ኡጋንዳዊው ተከላካይ ሳቪዮ ካቡጋ ነው።የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተከላካይ የሆነው ሳቪዮ የሰበታዎችን ተከላካይ ክፍል ሊያጠናክር እንደሚችል ይገመታል።
ጥቅምት 23 በሚጀምረው የአዲስ አበባ ዋንጫ ሚሳተፋት ሰበታ ከተማዎች በዘንድሮው የኢትዮጵይ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።
አስተያየት ይስጡ