አዲስ አዳጊዎቹ ሰበታ ከተማዎች የክረምቱ ፈራሚዎቻቸውን ቁጥር ወደ 5 ከፍ ያደረጉላቸውን የሁለት ተጫዋቾችን ፊርማ አጠናቀዋል።ውበቱ አባተን በዋና እሰልጣኝነት ለመቅጠር የተስማሙት ሰበታዎች የቀድሞው የሙገር ሲሚንቶ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ወልድያና መከላከያ አጥቂ ፍጹም ገብረማርያም በማስፈረም ለሚቀጥለው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ የሆነው ወንድይፍራው ጌታሁን(ቦልተና) ሰበታ ከተማን የተቀላቀለው ሌላ ተጨዋች ነው።
ሰበታዎች ከዚህ ቀደም በሃይሉ አሰፋና አዲስ ተስፋዬን ሲያስፈርሙ፤የነባር ተጨዋቾቹ ጌቱ ሃይለማርያም፣ፍርድአወቅ ሲሳይ፣ታደለ ባይሳና ኢብራሂም ከድር ውል ለአንድ ዓመት ማራዘም ችሏል።
አስተያየት ይስጡ