ሰበታ ከተማ የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

 

በዝውውር መስኮቱ ምንም አይነት እንቅስቃሴን ሳያደርጉ የቆዩት ሰበታ ከተማዎች የግራ መስመር ተካላካዩን ሀይለ ሚካኤል አደፍርስ ውልን ማራዘማቸው ተገልጿል ።

በአሰልጣኝ ውበተ አባተ የሚመሩት ሰበታ ከተማዎች እስከ አሁን ባለው የዝውውር መስኮት ምንም ተሳትፎን ያላደረጉ ሲሆን ከታዳጊው ቡድን ማደግ የቻለውን የግራ መስመር ተጫዋቹን ሀይለሚካኤል አደፍርስ ውል ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በማራዘም የዝውውር መስኮቱን ተቀላቅለዋል ።

ሰበታ ከተማ ሊጉ በኮሮና ቫይረስ እስከ ተቋረጠበት ወቅት ድረስ ሊጉን በ ሀያ ሁለት ነጥቦች አስረኛ ደረጃ ላይ ይገኙ ነበር ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor