ሰበታ ከተማ በሜዳው ጨዋታዎችን ሊያደርግ ነው !
በዘንድሮው የውድድር አመት ፕርሚየር ሊጉን በመቀላቀል ትልልቅ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በመያዝ በሊጉ ትላልቅ ቡድኖችን በመፈተን በውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ሰበታ ከተማዎች በሜዳቸው ሰበታ ስታዲየም ለመጫወት ተቃርበዋል ::
የመጀመሪያውን ዙር ሙሉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም የተጫወቱት ሰበታዎች ሊጉ ዳግም የሚጀምር ከሆነ ጨዋታቸው በሜዳቸው እና በደጋፊዎቻቸው ፊት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ::
ይህም ቡድኑ ከደጋፊዎች ያገኝ የነበረውን የስታዲየም ገቢ ከፍ ሲያደርግ ለቡድኑ ትልቅ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን ይጠበቃል ::
ሰበታ ከተማ በፕርሚየር ሊጉ በ 22 ነጥቦች አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ከመሪው ፋሲል ከተማ በስምንት ነጥቦች ብቻ ርቀው ይገኛሉ ::