ሰበታ ከተማዎች በተጨዋቾቻቸው ተወጥረዋል

 

አሰልጣኙም በ2013 ለመቀጠል ቅደመ ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ የሰበታ እግር ኳስ ክለብ ካለበት የፋይናንስ ሂሣብ ችግር ተሳቆ የሚጠበቅበትን ክፍያ ለመፈፀም እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ምንዳ በተለይ ለሀትሪክ እንደገለፁት “የፋይናንስ ችግር የለብንም ነገር ግን የውስጥ ገቢ ጉዳይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ገና ከያዝነው ሀምሌ ወር ጀምሮ ነው የሚሰበሰበው ገንዘቡ ገና ተጠናቆ ገቢ አልሆነም፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባውን ጨምር ደመወዙን ለመክፈል እየተረባረቡ ነው፤ ነገር ግን ገንዘቡ ተጠቃሎ ባለመግባቱ ያንን መክፈል አልቻልንም” ስሉ ይናገራሉ፡፡

እንደ አቶ አለማየሁ አስተያየት ከክለባችን ፕሬዚዳንት ጋር በመሆን ብዙ ቢሮ ውስጥ ገብተን እንደሚከፈል ተነግሮናል” ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልፀዋል፡፡ ሀትሪክ ከተጨዋቾች ባገኘችው መረጃ ግን የ2 ወር ደመወዝ፣ የ6 ወር ኢሴንቲቭና ሌሎች ቦነሶች አልተከፈለንም በዚህም ከፍተኛ ቅሬታ ውስጥ ነን ያለነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አንዴ ከ6 ወሩ የ4 ወሩን ሰርዙና የሁለት ወር ኢንሲቲቩን እንስጣችሁ ብለው ስንስማማ ቆይተው ደግሞ የ1 ወር ኢንሴንቲቭ ነው የምንሰጣችሁ እያሉ እያጉላሉን ከአንድም ሁለቴ ሄደን ብናናግራቸውም ክፍያውን ሊፈፅሙልን አልቻሉም በማለት ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለባቸው ለሀትሪክ አስረድተዋል፡፡

በርካታ ክለቦች ከተለመደው የ50 ሺህ ብር የደመወዝ ጣራ በላይ ከመጋረጃ ጀርባ ክፍያ ይፈፅማሉ እናንተስ ከዚህ ነፃ ናችሁ የተባሉት አቶ አለማየሁ በፍፁም አይታሰብም ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ በተደጋጋሚ ከተጨዋቾቹ ጋር ተነጋግረን ከክለቡ ጋር ተስማምተዋል እስከ ባለፈው 3 እና 4 ቀናት ድረስ ከአምበሉና ከተወሰኑት ተጨዋቾች ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበረኝ በርግጥ መነጋገር ያለብን ጉዳዮች አሉ የፌዴሬሽኑ የደመወዝ ጣሪያ ሕግ በፍፁም አንጥስም አክብረንም እየሰራን ነው፤ የ2 ወር ደመወዝ አለብን እስከ መጋቢት ድረስ ደግሞ ያለብንን ኢንሴንቲቭ እንከፍላለን ከዚያ ውጪ ምንም ማድረግ አንችልም ሊጉ ሲቆም የመጨረሻ ጨዋታችን መጋቢት መጀመሪያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረግነው ነው፤ እዚያ ድረስ ያለው ቦነስና ኢንሴንቲቭ መክፈሉ የግድ ነው፤ ነገር ግን ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ምንም በሚል ክፍያው ይፈፀም ይሄ ነው እውነታው፡፡

በነገራችን ላይ ደመወዝ እኛም አልተከ ፈለንም ሁላችንም ደመወዙን እንጠብቃለን በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከተጨዋቾቹ መሃል በተገኘ መረጃ የ2 ወር ደመወዝ የ6 ወር ኢሴንቲቭና ቦነስ አልተከፈለንም ያለብን የ2013 ውል ይነሳልን ጉዳጽ እያጋጠመን ነው በማለት ለፌዴሬሽን ደብዳቤ ለማስገባት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ለሀትሪክ የደረሳት መረጃ ያስረዳል፤ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ 2013 እንድቀጥል የሚሟሉልኝ ነገሮች አሉ በሚል ቅድመ ሁኔታ የቀረበላቸው የሰበታ ከተማ እግር ኳስ አመራሮች ከተጨዋቾቻቸው እየገጠመ ያለው ተቃውሞ እንዴት ያስማሙት ይሆን ለሚለው ጥያቄ የሚሰጡትን ምላሽ በርካቶችን እየጠበቁት ነው፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport