መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና “ሰበታ ከተማን በልጠን ከመጫወታችን አንፃር ሽንፈቱ አይገባንም” ዓለም አንተ ካሳ (ኢት.ቡና)�
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“ሰበታ ከተማን በልጠን ከመጫወታችን አንፃር ሽንፈቱ አይገባንም” ዓለም አንተ ካሳ (ኢት.ቡና)�

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ
ከተማ የ/ሲቲ ካፕ/ መክፈቻ ጨዋታው በሰበታ
ከተማ ሽንፈትን አስተናግዷል፤ ግጥሚያውን
እንዴት አገኘኸው?
አለምአንተ፡- የሰበታ ከተማ ክለብን
በተፋለምንበት የእሁዱ ጨዋታ ምንም እንኳን
በጠባብ ውጤት ሽንፈትን ብናስተናግድበትም
በሜዳ ላይ የነበረን እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ
እና በተጋጣሚያችንም ላይ የጨዋታን ብልጫ
የወሰድንበት ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ቡድናችን
በጨዋታው ላይ ጥሩ ሆኖ ሳለ የጎል ማግባቱ
ላይ ችግር የነበረበት ነውና ይሄን በሂደትና
በቀጣይነት የምናሻሽለው ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ቡና እና የሰበታ
ከተማ የእሁዱ ጨዋታ ላይ የነበራችሁ
ጠንካራና ደካማ ጎን ምን ነበር?
አለምአንተ፡- ሰበታ ከተማን
ስንገጥም የቡድናችን ጠንካራ ጎን ነው ብለን
የምናስበው ብዙ ኳስ መያዝ መቻላችን
መከላከል ጭምር ነው ብለን ስለምናምን
ያን በእንቅስቃሴያችን ላይ ተግባራዊ
በማድረግ አሳክተናል፤ በጨዋታውም
ላይ ብዙ ኳሶችን ይዘን ፖሰስ በማድረግ
መጫወታችንም ጥቅሙን አይተንበታልና
ይሄን ነው በቀጣይነትም ልናስቀጥል
የሚገባን፤ የቡና የእሁዱ ድክመት ተብሎ
ሊጠቀስ የሚገባው ወደ ተቃራኒ ቡድን የሜዳ
ክልል ከገባ በኋላ እና ጎል ጋርም ከደረሰ
በኋላ በማስቆጠሩ ላይ ችግር ነበረበት፤ ከዛ
ውጪም በተደጋጋሚ የእነሱን የመከላከል
አጨዋወትም በምን መልኩ ማስከፈት
እንዳለበትም የሚጎለው ጥቂት ነገሮችም
አሉና እነዛን በቡድን እንቅስቃሴ አጨዋወቶች
ውስጥ አስተካክለናቸው የምንመጣቸውም
ይሆናሉ፡፡
ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና በሰበታ ከተማ
ተሸንፏል፤ ሽንፈቱ አበሳጭቷቸዋል?
አለአለም፡- በሰበታ ከተማ ክለብ
ያስተናገድነው የእሁድ ዕለቱ ሽንፈት እኛን
ከማበሳጨት ይልቅ በጣም ያስቆጨን ነበር፤
ያስቆጨን መሸነፍ ስላልነበረብን ነው፤
ምክንያቱም በሜዳ ላይ ከነበረን “ ከጨዋታ
ባሻገር በውጤትም ጭምር የምናስደስትበት
ጊዜ ሩቅ ስለማይሆን ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የእሁድ ተጋጣሚያችሁ
ስለነበረው የሰበታ ከተማ ክለብ አቋም
ምን ትላለህ?
አለምአንተ፡- የሰበታ ከተማ ክለብ
በአገራችን የእግር ኳስ ክንውን ውስጥ
ብዙ ልምድ እና ጥሩም ስብህና ያላቸውን
ተጨዋቾች ከመያዙ አኳያ በመልካም
ቡድንነቱ ልንጠቅሰው ብንችልም ከእኛ ጋር
ባደረገው ጨዋታ ግን በቡድን ስራ አጨዋወት
የኳስ ብልጫ ተወስዶበት የወጣ ቡድን ነበርና
እነሱን እንደጠበቅኳቸው አላገኘዋቸውም፡፡
ሀትሪክ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ባደረግከው
የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ
ጨዋታህ የግጥሚያው ኮከብ ተጨዋች
ተብለህ ተሸልመሃል፤ በመሸለምህ ምን አይነት
ስሜት ተፈጠረብህ? በጨዋታው ላይስ ራሴ
ሙሉ ተጨዋች ነበርኩ ብለህ ታስባለህ?
አለምአንተ፡- የሰበታ ከተማ ክለብ ጋር
በነበረን እና ሽንፈትን ባስተናገድንበት የእሁድ
ዕለቱ ጨዋታ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ከሞላ
ጎደል ጥሩ ብቃቴን ለማሳየት ችያለው፤ ጥሩም
ለመንቀሳቀስ ስለቻልኩ የጨዋታው ኮከብ
ተብዬ ለመሸለም በቅቻለው፤ በዕለቱም ኮከብ
ተብዬ በመሸለሜም በጣም ነው የተደሰትኩት፤
ይህ ሽልማት ግን የእኔ ብቻ ሳይሆን የቡድኔ
ተጨዋቾችም ጭምር ነው፤ የክለባችን ሙሉ
ተጨዋቾች እና ክለባችንም በጥሩ ብቃት ላይ
ስለተገኙም ነው እኔ ጎልቼና ኮከብም ልባል
የቻልኩትና ሽልማቱን በተመለከተ ለእኔም
ለቡድኔ ተጨዋቾችም እንደዚሁም ደግሞ
ለኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎች ጭምር
መታሰቢያነቱ ይሁንልኝ ብያለው፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ከሰበታ ከተማ ጋር
ባደረገው ጨዋታ ጥሩ ለመንቀሳቀስ ብችልም
ሙሉ ተጨዋች ነበርኩ ብዬ ለመናገር ግን
በፍፁም አልደፍርም፤ ምክንያቱም በአዲሱ
የክለቡ አጨዋወት ውስጥ የሚቀረኝ ብዙ
ነገር አለና እነዚህንም ከአሰልጣኞቼ ምክር
በመስማትና ያሉብኝንም ክፍተቶቼን
አስተካክዬ በመምጣት የቡድኑ ሙሉ አቅም
ያለው ተጨዋች እንደምሆን አስባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ቡና አዲሱ
አጨዋወት ተመችቶሃል?
አለምአንተ፡- በጣም እንጂ ፤
በመጀመሪያው ጨዋታችን ጥሩ ኳስን ነው
የተጫወትነው፤ በቀጣይነት ደግሞ ጨዋታው
ትዕግስትን ስለሚፈልግ ይበልጥ አሻሽለነው
በመምጣት ብዙዎችን በኳስም በውጤም
የምናስደስታቸው ይሆናል፡፡
አለምአንተ፡- የኢትዮጵያ ቡና
ደጋፊዎችን የእሁዱ ጨዋታ ላይ በምን
መልኩ ተመለከትካቸው.. አንተንስ እንዴት
እንጠብቅህ
አለምአንተ፡- የቡና ደጋፊ የእሁዱ
ጨዋታ ላይ ትህግስት አድርጎ ነበር ሲደግፈን
የነበረው፤ በቀጣይነትም በዚህ እንዲቀጥሉ
ነው የምንፈልገው፡፡ በዘንድሮ ውድድርም
የቡና ደጋፊ እኔን በጥሩ ነገር ይጠብቀኝ
ወጣት ተጨዋች ከመሆኔ አኳያም ትላንት
ከነበረኝ ብቃት የበለጠ አቅሜን አውጥቼ
እጫወታለው፡፡ ሀ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...