ሰበር ዜና | ቅዱስ ጊዮርጊስ ቆራጥ እርምጃ ወስዷል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኙን ሰርዳን ዝቭጂኖቭን ጨምሮ ሌሎች የአሰልጣኝ አባሎቻቸውን አግደዋል።

 

ከቀናት በፊት ከክለቡ አባላት ጋር ውይይት ያደረገው ክለቡ ለውጤት መጥፋት ምክንያት ናቸው ያላቸውን አባላት ከስራ አግዷል። በዚህም መሰረት

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ እና ረዳቶቻቸውን ጨምሮ የታገዱ ሲሆን። የቴክኒክ ኮሚቴውም በይፋ ሲፈርስ የቡድን መሪ እና ስራ አስኪያጅ በነበሩት አቶ ሰለሞን በቀለ ምትክ በቦታው ከዚህ ቀደም የነበሩት አቶ ታፈሰ እንዲሾሙ ተደርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ነገ በ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ ከሰበታ ከተማ ጋር የሚገጥም ሲሆን ሲኔየር ተጫዋቾች እርስ በእርሳቸው ተመራርጠው ጨዋታውን እንዲያከናውኑ ተደርጓል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport