ቢያድግልኝ ኤልያስን ከጅማ አባ ቡና እንዲሁም ሰለሞን ገብረመድህንን ከፋሲል ከተማ አስፈርሟል
በ 2009 የፋሲል ከተማ ስብስብ ውስጥ 1 ዓመት ቆይታ ያደረገው ሰለሞን ገብረመድህን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለመተሐራ ስኳር ለሰበታ ከተማ ለኢትዮጵያ ቡና እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድኖች በመሀል ሜዳ ስፍራ ላይ እግር ኳስን በመጫወት ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ሰለሞን ገብረመድህን በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ወልዲያ ከተማን በመቀላቀል ከአሰልጣኙ ጋር ዳግም በወልድያ ከተማ ይገናኛሉ።
በ 2009 የውድድር ዘመን በጅማ ከተማ ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ የቻለው ቢያድግልኝ ኤልያስ ለ 1 ዓመት ቆይታ በኋላ ክለቡን ለቆ ወልድያ ከተማን ተቀላቅሏል።
ባሳለፍነው ሳምንት ወልድያ ከተማን የተረከቡት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ክለቡን ለማጠናከር በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
አስተያየት ይስጡ