መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ፈረሰኞቹ አሜ መሀመድ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ከመሪው ደደቢት ያላቸውን የነጥብ ልዩነት አጥበዋል
ሪፖርትሲዳማ ቡናቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ፈረሰኞቹ አሜ መሀመድ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ከመሪው ደደቢት ያላቸውን የነጥብ ልዩነት አጥበዋል

አጋራ
አጋራ

በሜዳቸው ሲዳማ ቡናን ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ በአሜ መሀመድ ብቸኛ ግብ ወደ መሪዎቹ የተጠጉበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በ19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲዬም ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ በባለሜዳዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡በሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የየባለሜዳው ቅ/ጊዬርጊስ ተጨዋቾች “ቅድሚ ለሰብዓዊነት” የሚል ትልቅ ባነር ይዘው የክለቡ ደጋፊ ለሆነው እና በኩላሊት ህመም ለሚሰቃየሁ ዘካሪያስ ተፈሪን ለማስታወስና ለማሰብ የልጁ ፎቶ የታተመበት ነጭ ቲሸርት ለብሰው ወደ ሜዳ በመግባት የገንዘብና ሌሎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ይህም የሚቀጥል ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

ጨዋታው ሲጀምር ፈረሰኞቹ በአፍሪካ ኮንፌደሬሺን ዋንጫ ባለፈው ሳምንት የኮንጎውን ካዛ ብራዛቪል ካሸነፉበት የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች የግብ ተባቂ ለውጥ ብቻ ሲያደርጉ ኦዶንካራን አሳርፈው ለአለምን በመተካት ወደ ሜዳ ሲገቡ እንግዳዎቹ ሲዳማዎች በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ካሸነፉበት የመጀመሪያ ተሰላፊዎች የ1 ተጨዋች ለውጥ ሲያደርጉ ዬሴፍን በወንድሜነህ በመተካት ገብተዋል፡፡

በጨዋታው የፈረሰኞቹ የቀድሞ ተጨዋች ፍፁም ተፈሪ ሲዳማ ቡናን በአንበልነት እየመራ የቀድሞ ክለቡን ሲገጥም በተቃራኒው የቀድሞ የሲዳማ ቡና ተጨዋች ሙላለም መስፍን የቀድሞ ክለቡን በገጠመበት በዚህ ጨዋታ በርካታ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች የጨዋታው ውበት ሁነው አምሽተዋል፡፡

የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ሲጀምር በፈረሰኞቹ በኩል ጨዋታውን ለማሸነፍ ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ እና በተጋጣሚያቸው ላይ ጫና ለመፍጠር ሲመሞክሩ ገና በ1ኛው ደቂቃ ወደ ተጋጣሚያቸው ግብ በመድረስ የማዕዘን ምት ማግኘት ችለዋል፡፡በጨዋታው ሂደት እንግዳዎቹ ሲዳመማዎችም ከጨዋታው ነጥብ ለመጋራት ጥሩ በተንቀሳቀሱበት በዚሁ አጋማሺ ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ገና በ4ኛው የደቂቃ የፈረሰኞቹ ተከላካዮች በሰሩት ስህተት ያገኙት ኳስ ሳይጠቀሙበት ቀሩ እንጂ ወደ ግብነት ሊቀዬር የሚችል ነበር፡፡

ፈረሰኞቹ የተሞከረባቸውን የግብ ሙከራ ለማስቆምና ተጋጣሚያቸው ወደ ራሱ የግብ ክልል ተመልሶ እንዲጫዎት ለማድረግ በተደጋጋሚ ወደ ቡናዎች የግብ ክልል በመግባት ጥሩ የማግባት ሙከራዎችን ሲያደርጉ በ13′ እና በ21′ በመሃሪ መና አማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡በቡናዎች በኩል የጠሩ የግብ ማግባት ሙከራዎችን ማድረግ ሳይችሉ፡፡ ቅዱስ ጊዬረርጊሶች በ36ኛው ደቂቃ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ አሜ መሀመድ ወደ ግብነት በመቀየር ፈረሰኞቹን መሪ ማድረግ ችሏል፡፡

ሲዳማ ቡናዎች ከግቧ መቆጠር በሇላ የአቻነት ግብ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ በ38′ ደቂቃ ለአለም ካመከነባቸው ኳስ ሌላ ያን ያህል የጠራ የግብ ዕድል ሳይፈጥሩ፡ተጋጣሚያቸው በተመሳሳይ ከግቧ መቆጠር በሇላ ሌላ የግብ ሙከራ ሳያደርጉ የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ እንግዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች የአቻነት ግብ ለማግኘት በተንቀሳቀሱበት በዚሁ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የሜዳ ላይ እንቀቅስቃሴ ስንመለከት ቡናዎች በ54′ ለግብ የተቃረበ ሙከራ ሲያደርጉ፡ፈረሰኞቹ አልፎ አልፎ የሚፈጥሯቸውን የግብ ኳሶች በአግባቡ ሳይጠቀሙባቸው ሲመክኑ አምሽተዋል፡፡በተለይም 63ኛው ደቂቃ በአሜ መሀመድ የግል ጥረት ወደ ግብ የተመታችው ኳስ በሲዳማው ግብ ጠባቂ የመከነችበት ድንቅ ሙከራ ነበር፡፡

ፈረሰኞቹ አቡበከር ሳኒን አስወጥተው ናትናኤል ዘለቀን እንዳሁም በበሀይሉ አሰፋ አዳነ ግርማን በመቀየር የተጨዋቾች ቅያሪ በማድረግ የቦታ ለውጥ ሚና በማድረግ ሲጫዎቱ አዳነ ወደ ሜዳ ከገባበት ደቂቃ በሇላ በመሃል አጥቂነት ሲጫዎት አብዱልከሪም ወደ መስመር ወጥቶ በተጫዎተበት ምሺት በሁለቱም ቡድኖች ለተመልካች የሚማርክ እንቅስቃሴ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡

ብዙም የጠሩ የግብ ሙከራዎች በሌሉበት የሁለተኛው አጋማሽ ፈረሰኞቹ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ወደ ግብ ክልላቸው ተመልሰው ተከላክለው ውጤታቸውን ለማስጠበቅ ሲጫዎቱ ሲዳማዎች ተደጋጋሚ የግብ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም የጠሩ ሙከራዎች አልነበሩም፡፡በዚህም በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ጎል ሳይቆጠር ባለሜዳዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ በአሜ መሀሙድ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ ጣፋጭ ድል ማስመዝገብ ሲችሉ ከመሪው ደደቢት ያላቸውን የነጥብ ልዩነት 1ተስተካካይ ቀሪ ጨዋታ እያላቸው ወደ 3 ነጥብ ማጥበብ ችለዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...