መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ዋልያዎቹ በሜዳቸው በሩዋንዳ ተሸንፈዋል
ሪፖርትዜናዎች

ሪፖርት | ዋልያዎቹ በሜዳቸው በሩዋንዳ ተሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

 

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ቻን 2020 ማጣሪያ በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም የሩዋንዳ አቻውን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠረበት ግብ ተሸንፏል።

በ4-3-3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ዋልያዎቹ በመጀመርያው አጋማሽ ከተጋጣሚያቸው የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም የፈጠርዋቸው የግብ አድሎች አናሳ መሆናቸው አንዲሁም አልፎ አልፎ የሚገኙት አድሎችን በአግባቡ አለመጠቀማቸው የመጀመርያ አጋማሹን ያለግብ አንዲያጠናቅቁ አድርጓቸዋል።

ደስታ ደሙ ከቀኝ መስመር አሻምቶት ፍቃዱ አለሙ በግምባሩ መትቶት ወደ ውጪ በወጣ ኳስ የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ ያደረጉት ዋልያዎቹ ካስ ከኃላ ለመመስረት ያደረጉት ሙከራ ጥሩ ሚባል ቢሆንም ኳሶቹ ወደ ሜዳው የመጨረሻ ክፍል ሲደርሱ በተጨዋቾቹ የነበረው አለመግባባትና ጠጋግቶ አለመጫወት በቀላሉ በሩዋንዳ ተከላካይ ክፍል ቁጥጥር ስር አንዲውሉ አድርጓቸዋል።

የመጀመርያው አጋማሽ ሌላኛው ተጠቃሽ ሙከራ ከንአን ማርክነህ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን በቀኝ በኩል ያገኘውን ኳስ መሬት ለመሬት ቢመታውም የሩዋንዳው ግብ ጠባቂ ኤሪክ ሚሻሚና ሊመልሰው ችሏል።

ከጨዋታው የመጀመርያ 15 በኃላ የማጥቃት ሃይላቸውን ወደ ግራ መስመር ያዞሩት ዋልያዎቹ በ20ኛው ደቂቃ አህመድ ረሺድ ከአማኑኤል ጋር በጥሩ ቅብብል አልፎ ያሻማው ኳስ ወጣቱ አጥቂ መስፍን ታፈሰ ቢመታውም በሩዋንዳ ተከላካዮች ሊመለስ ችሏል።

ግራ መስመር ላይ ትኩረት ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጨዋወት በ25ኛው ደቂቃ በተመሳሳይ አህመድ ረሺድ ከአማኑኤል ዮውሃንስ የተሰጠውን ኳስ በቀጥታ ቢያሻማውም በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ የነበረው አማኑኤል ገብረሚካኤል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ አጋማሽ የመጨረሻ ሙከራ በሃይደር ሸረፋ አድርገዋል፤በግራ መስመር የተገኘውን ቅጣት ምት አማኑኤል ገብረሚካኤል አሻምቶት ከንአን ወደ ውስጥ የመለሰው ኳስ ሃይደር ጋር ደርሶ ለግቡ ቅርብ የነበረው ሃይደር ቢመታውም ተከላካዩ አንጃም ሚስታንዚ ተደርቦ ሊመልሰው ችሏል።

ከቆሙ ኳሶችና ከመስመር በመነሳት አድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ የታዩት ሩዋንዳዎች የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራቸውን ለማድረግ 38 ደቂቃዎችን ጠብቀዋል።አማኑኤል አማንሺ ከግራ መስመር ያሻማው ኳስ በጃኮ ኦራንዚ ቢመታውም ምንተስኖት አሎን ሚፈትን አልነበረም።

ሁለተኛው አጋማሽ አንደተጀመረ ማጥቃታቸውን የጀመሩት የአብርሃም መብራህቱ ልጆች በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያ 5 ደቂቃዎች ላይ ሁለት እድሎችን በመስፍን ታፈሰና አማኑኤል ገብረሚካኤል ቢፈጥሩም አሁንም ንቁ ሆነው ሲከታተሉ በነበሩት የሩዋንዳ ተከላካይ ክፍል ተጨናግፎባቸዋል።

ከመጀመርያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ በሁለተኛው አጋማሽ ለማጥቃት የሞከሩት ሩዋንዳዎች በ61ኛው ደቂቃ በኤርነስት ሴጉራ አማካኝነት የጨዋታው ብቸኛና የማሸነፍያ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።ግራ መስመር ላይ የተገኘው ቅጣት ምት ኢራንዚ ጄሲ ሲያሻማው ፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በቀኝ በኩል የነበረው ማንዚ ቲየራ የኢትዮጵያ ተጨዋቾች ማራቅ ያልቻሉትን ኳስ ወደ ውስጥ አሻግሮት በነፃ አቋቋም የነበረው ኤርነስት ሴጉራ በመቀስ ምት ድንቅ ግብ ማስቆጠር ችልዋል።

ከግቡ መቆጠር በኃላ መረጋጋት የተሳናቸው ዋልያዎቹ በ62ኛው ደቂቃ ኳስን ከኃላ ለመመስረት በሚሞክሩበት ጊዜ በፈጠሩት ስህተት ኢራንዚ ጄሲ ያገኘውን ኳስ በግምት ከ20 ሜትር አካባቢ አክርሮ የመታው ኳስ ምንተስኖት አሎ ወደ ውጭ አውጥቶበታል።ከግቡ መቆጠር በኃላ በፍቃዱ አለሙን በአዲስ ግደይ፣አስቻለው ግርማን በመስፍን ታፈሰ፣ከንአን ማርክነህን በሙጂብ ቃሲም ቀይረው ያስገቡት አብርሃም መብራህቱ በመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ አቻ ሊያደርጋቸው የሚችሉ እድሎችን በአማኑኤል ገብረሚካኤል፣ያሬድ ባዬ፣ሙጂብ ቃሲም አና ደስታ ደሙ አማካኝነት ቢያገኙም የሩዋንዳን ግብ ክልል መድፈር ተስንዋቸው ታይቷል።በተለይ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ከቀኝ መስመር እየተነሳ ማጥቃት ላይ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ደስታ ደሙ በ86ኛው ደቂቃ ላይ በግምት ከ15 ሜትር አካባቢ የመታው ኳስ የግቡ ቀዋሚ ብረት ሊመልስበት ችልዋል።

በዚህም መሰረት ጨዋታው በአንግዳው ቡድን ሩዋንዳ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችልዋል።የመልሱ ጨዋታ ከአንድ ወር በኃላ ኪጋሊ ሩዋንዳ ላይ ይካሄዳል።

የአሰልጣኞች አስተያየት

አብርሃም መብራህቱ

“የመጀመርያው 45 አንግዲህ አንደተመለከታቹት አንሱ ሙሉ በሙሉ በመከላከል ላይ ያመዘነ አጨዋወት ነበር ሚጫወቱት ያንን ሰብሮ ለመግባት እና ደግሞ መጀመርያ ላይ ያገኘናቸው አጋጣሚዎች መጠቀም አለመቻላችን የተጨዋቾቻችን በራስ መተማመን ትንሽ አንዲወርድ አድርጎታል።በሁለተኛው አጋማሽ ያለውን ነገር አርመን ብልጫ ወሰደን ብዙ ሞክረናል አልተሳካልንም።ሁለተኛ ደግሞ ቀይረው የገቡት ተጨዋቾች ልዩነት ፈጥረዋል በቡድኑ ላይ በተለይ በማጥቃቱ ረገድ ላይ።

ውጤቱን የመቀልበስ እድል

“የመቀልበስ እድሉ አለን።ብዙ ብልጫ ሳይወሰድብን በጥቃቅን ስህተቶች ነው ግቡ የተቆጠረብን።ከዚህ ውጪ ግን እጅግ በጣም አስፈሪ የሚባል ነገር አልገጠመንም።ስነ ልቦና ላይ ሰርተን የመልሱ ጨዋታ ለማሸነፍ አንዘጋጃለን።

የወዳጅነት ጨዋታ ስላለማድረጋቸው

” የሩዋንዳ ቡድን አንደኛው ረጅም ጊዜ አብረው መቆየታቸው አንዱ ጥንካርያቸው ነው፤ሁለተኛው ደግሞ ከሥስት በላይ የወዳጅነት ጨዋታ ማድርጋቸው ቅንጅት ላይ ጠቅሟቸዋል።እኛ ደግሞ በአንፃሩ ልጆቻችን በሚገባ ያላቸውን ልምድና ቅንጅት አንዳይጠቀሙ አድርጎታል።ስለዚህ በቀሪው የአንድ ወር ዝግጅት በተቻለ መጠን የወዳጅነት ጨዋታ ልናገኝበት የምንችል መንገድና ያሉንን ስህተቶች አይተን ቡድናችንን ገንብተን ወደ ሩዋንዳ ምንሄድበት ምክንያት አንፈልጋለን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...