መነሻ ገጽ ሪፖርት ​ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጪ የመጀመሪያ ድሉን ድሬ ላይ አስመዝግቧል፡፡
ሪፖርትዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጪ የመጀመሪያ ድሉን ድሬ ላይ አስመዝግቧል፡፡

አጋራ
አጋራ

በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ድል እርቆት የቆየው ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 2-0 አሸነፈ፡፡  ይህንንም ተከትሎ
ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጪ ያስመዘገበው የመጀመሪያው ነጥብ ሲሆን ድሬዳዋ ከተማ በአንፃሩ በሜዳው ያስተናገደው የመጀመሪያው ሽንፈቱ ሆኗል።

በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ወደ ግብ በመድረስ ኢትዮጵያ ቡና የተሻሉ ነበሩ፡፡

በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል የተሰተናገደው በ64ኛ ደቂቃ ላይ  ሳሙኤል ሳኑሚ ኢትዮጵያ ቡናን ቀዳሚ ሲያደርግ ከግቧ መቆጠር በኃላ ድሬዳዋ ከተማ  አልፎ አልፎ ግብ ለማስቆጠር ጥረት አደርገዋል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ  በባከነ ሰዓት 90+3 ደቂቃ ላይ አማኑኤል ዮሐንስ ሁለተኛ ጎል ለቡናማዎቹ በማስቆጠር  በቡዱኑ ውጤት የተከፋውን ደጋፊ ያሰደሰተ ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ከጨዋታው በኋላ የድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች በክለቡ ውጤት በመበሳጨታቸው ተቃውሞአቸውን በስታዲየሙ ውስጥ ገልጸዋል፡፡

 

የአሰልጣኞች አስተያየት 

አሰልጣኝ ስምዖን አባይ-ድሬዳዋ ከተማ

” ለክለቡ ሽንፈት ኃላፊነቱን እወስዳለሁ:: ደጋፊውንም ይቅርታ እጠይቃለሁ :: በጨዋታው  ይዘን የገባነውን ስልት ተጫዋቾቼ 10 ከመቶውን እንኳን መተግበር ባለመቻላቸው ልንሸነፍ ችለናል፡፡በቀጣይ ሳምንት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በምናደርገው ጨዋታ የተሻለ ሥራ በመስራት አሸንፈን ደጋፊውን ለመካስ እንጥራለን”
 አሰልጣኝ ዲድየ ጎሜዝ

 “በጨዋታው  ያገኘናቸውን  እድሎች ወደ ጎል በመለወጥ ሙሉ ሶስት ነጥብ ማግኘታችን አሰደስቶናል፡፡ ያስመዘገብነወሸ ውጤት  እረጅም  ኪ/ሜ አቋርጦ በሙሉ ዘጠና ደቂቃ ክለባቸውን ሲደግፉ  ለነበሩ ሁሉ ወሳኝ  ነበር፡፡ በቀጣይም ቡድናችን ዛሬ ባገኘው ውጤት በመነቃቃት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን፡፡”

በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ድሬ ከነማ በመጪው እሁድ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር አርባ ምንጭ ላይ ይጫወታል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...