መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | በደቡብ ደርቢ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን  አስተናግዶ 3ለ1 በማሸነፍ የመጀመርያውን 3 ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
ሪፖርትሲዳማ ቡናወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | በደቡብ ደርቢ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን  አስተናግዶ 3ለ1 በማሸነፍ የመጀመርያውን 3 ነጥብ አስመዝግቧል፡፡

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ተኛ ሳምንት ጫዋታ ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ዲቻ ያገናኘው ጫወታ  ከመጀመሩ በፊት የሁለቱ  ክለብ ደጋፊዎች  ለቡድን መሪ እና አሰልጣኞች የባህል አልባሳት ስጦታ በማበርከት ነበር፡፡

ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉ የ2ተኛ ሳምንት በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ትርታዬ ደመቀ  ቅጣቱን አልጨረሰም በማለት ወላይታ ደቻዎች ክስ አስመዝግበው ነው ጫወታ የተጀመረው፡፡
በጨዎታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ ወደ ግብ በመድረሱ የተሻሉ ነበሩ የመጀመርያው ግብ በ9ኛው ደቂቃ  ትርታዬ ደመቀ ከማዕዘን ያሻማውንኳስ አብዱልላጢፍ መሐመድ በጭንቅላት ግብ ከመረብ አሳርፏት ባለ ሜዳዎቹን መሪ አርጓቸዋል፡፡ ከግቧ መቆጠር በሗሏ ሲዳማ ቡናዎች በይበልጥ ተጭነው  ቶሎቶሎ ወደ ግብ መድረስ ችለዋል በ16ተኛው ደቂቃ አብዱላጢፍ መሐመድ ያሻገረለት ኳስ ሀብታሙ ገዛህኝ በግንባሩ መቶ ግብ ጠባቂው ወንደሰን ገረመው አድኖበታ፡፡

በ21ኛው ደቂቃ አብዱላጢፍ መሐመድ የወላይታዲቻ ተነላካዮች በማታለል ያቀበለውን ኳስ ሀብታሙ ገዛህኝ ወደ ጎል ቀይሯት ባለሜዳዎቹ 2ለ0 መምራት አስችሏቸዋል፡፡

ከግቧ መቆጠር በሗላ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሆነ ሙከወከራ አልነበረም፡፡  በ38ኛው ደቂቃ ወላይታ ዲቻው  ተመስገን ዱባ ከርቀት የመታት ኳስ ወደ ውጪ ወታለች፡፡ በ41ኛው ደቂቃ የሲዳማ ቡናው ዮሴፍ ዮሐንስ ከርቀት የመታትን ኳስ ግብ ጠባቂው አድኖበታል፡፡በዚሁ ውጤት እረፍት ወጠዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ብዙም ማራኪ ባልነበረው እቅስቃሴ ነበር  የተጀመረው በ62ኛው ደቂቃ አብዱለጢፍ መሐመድ ጥፍት ተሰርቷል በማለት የተዘናጉት የዲቻ ተጫዋቾች አዲስ ግደይ  በፍጥነት በመቅደም ወደ ግብ ክልል ሲገባ የዲቻው ግብ ጠባቂ ጥፋት በመስራቱ የተሰጠው ፍ.ፁ.ም  አዲስ ግደይ አስቆጥሯል፡፡
በ64ተኛው  ደቂቃ ከጉዳት የተመለሰው የቀድሞው የሐዋሳ ከተማው ጃኮ አራፍት በያሬድ ዳዊትን  ተቀይሮ ወደ ሜዳ ከገባ በሗላ ጫና ፈጥሮ በመጫዎቱ ወላይታ ዲቻዎች ተሽለው ታይተዋል፡፡ በ75 ደቂቃ አምረላ ደልታታ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዳግም በቀለ በጭንቅላቱ ወደ ግብ ቀይሮታል፡፡

እንግዳዎቹ ከግቧ መቆጠር በሗላ በተሻለ መልኩ ወደ ፊት ተጭነው መጫዎት ቢችሉም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡በ78ተኛው ደቂቃ  ምስጋናው ወ/ዮሐንስ ከአብዱለጢፍ መሐመድ የተቀበለው ኳስ የግቡን ቋሚ ታካ ወደ ውጪ ወታለች፡፡ በዚሁ ጨዋታው በባለ ሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት

  አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ   

ደስ ብሎኛል ከከባድ ሽንፈት በሗላ  በደርቢ ጫወታ ማሸነፍ ቡድኔ  አቅም እንዳለው እና የልጆ  በጥቃቅን ስተቶች ነበር ምንሸነፈው እና ነጥብ ምናጣው  ፡፡ ዛሬ ግን ወስነን ገብተን አሸንፈናል ይህም የልጆቼን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡ ከዚህ  በፊትም ቡድናችን በእንቅስቃሴ የተሻለ ነው በራሳችን ጥቃቅን ክፍተቶች ነበር ነጥብ ምናጣው በአዲሱስ መንፈስ በአዲስ አስተሳሰብ ገብተን              የተነጋገርነውን ተግባራዊ አድርገውልኛል፡፡

መሳይ ተፈሪ ወላይታ ድቻ

” በመጀመሪያው አጋማሽ እነሱ ጥሩ ነበሩ በሁለተኛው አጋማሽ እኛ ጥሩ ነበርን ተሸንፈንም ወተናል፡፡ ያሰብነውን ማግኝት አልቻልንም ዛሬ በሙሉ ጥሩ አልነበርንም ሁልጊዜ ግን ማሰብ ያለብን ጉድለታችን ምንድነው ብለን ሰርተን መለወጥ አለብን ነገ ደግም አሸንፈን እንደምንመለስ አልማለው ጉዳቶች አሉብን ነገር ግን መደናገጥ የለብንም ነገ አሸንፈን ወደ ላይ ብቅ እንላለን ለነገ ማሰብም አለብን የተሻለውን ዲቻ በቀጣይ ጠብቁ::

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...