መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ሲዳማ ቡና ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
ሪፖርትሲዳማ ቡናኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ሲዳማ ቡና ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

አጋራ
አጋራ

በ 15ኛ ሳምንት የኢትዮጽያ ፕሪሜየር ሊግ ይርጋለም ስታድየም ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል ። 

ሲዳማ ቡና ቀድሞ ይጠቀማቸው ከነበረው 3 ተጫዋቾችን ለውጦ ሲገባ የመጀመርያው 45 ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ሳይደረግበት ብሎም የጨዋታ ፍሰት ሳይኖረው ያለቀ ሲሆን በ አመዛኙ ሲዳማ ቡና ተጭኖ በመጫወት ጥረት ማድረግ ችሏል። 

በጨዋታው  ሹክቻና ውጥረት የበዛበትና  ጨዋታውን  ለመቆጣጠር ለዳኞች  አስቸጋሪ የሆነ የመጀመሪያ  አጋማሽ ነበር። በ 37ኛ” ድቂቃ የ እንግዳው ቡድን የኤሌክትሪኩ  አምበል አዲስ ነጋሽ ከ ዳኛው ጋር ከልክ በላይ በመከራከሩ የ ቢጫ ካርድ ሰለባ ሆኖአል።በዚሁ ጨዋታው  የጎላ የጎል ሙከራ ሳይደረግበት ወደ መልበሻ ቤት አምርቷል ።

በ 2ኛው አጋማሽ  መጀመሪያ ተሽሎ የ ገባው ሲዳማ ቡና ገና ሁለትኛው 45 እንደተጀመረ  በ46ኛ  ደቂቃ ላይ የኤሌክትሪክ  ተከላካዮችን  ስህተት ተጠቅሞ ባዬ ገዛኸኝ ባለ ሜዳው ቡድን መሪ የሚሆንበትን ግብ አስቆጥሮ 1-0 መሪነት እንዲይዙ ሲያስችል። በአንጻሩ ኤሌክትሪኮች ከግቧ መቆጠር በኃላ ወደ ግብ በመጠጋት  ሙሉለሙሉ የበላይነትን መውሰድ ችለዋል።  በ 70 ኛ ደቂቃ ላይ  ተክሉ ተስፋዬን በ ሀይሌ እሸቱ  ቀይረው ማስገባት ችለዋል ። ከ ተክሉ መግባት በኅላ በተደጋጋሚ  ጫና መፍጠር የቻሉት  ኤሌክትርኮ በ 78ኛ ደቂቃ ላይ በተክሉ ተስፋዬ አማካኝነት የ አቻነቱን ግብ ማስቆጠር ችሏል  ። ከግቧ መቆጠር  በኃላ ውጤቱን ለመቀልበስ መሀመድ አብዱለጢፍን ፣አማሃ በለጠንና አዲሱ ተስፋዬን ቀይረው  ቢያስገቡም በውጤቱ ላይ ለውጥ ማምጣት አልቻሉም።ጨዋታው በዚሁ የአቻ 1-1 ውጤት ተጠናቋል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ  በኃላ የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች የስታዲየም በር በመዘጋት  ቅሬታቸውን አሰምተዋል። በክለባቸው  ውጤት ደስተኛ ያልሆኑት ደጋፊዎች  ከተወሰኑ አለመግባባቶች በኃላ ግጭቱ  በሰላም  በውይይት ተፈቷል።

የአሰልጣኞች አስተያየት 

አለማየሁ አባይነህ ~ሲዳማ ቡና

 ” በጨዋታው በተውሰነ መልኩ ቡድኔ ውስጥ አለመረጋጋት ነበረ። በተወሰኑ ተጫዋቾች ምክንያት ውጤቱን አጥተናል። በቀጣይ ዙር ከ ሜዳችን ውጪም በማሸነፍ ፉክክር ውስጥ እንገባለን ”                              

አሸናፊ በቀለ ~ኢትዮ-ኤሌክትሪክ 

“በተጋድሎም ቢሆን ከ ሜዳችን ውጭ 1 ነጥብ መውሰድ ችለናል  ።ለ ቀጣዩ 2ኛ ዙር ጠንክረን እንቀርባለን ።ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ከልጄቼ ጋር እንተጋለን ።”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...