በ 12ኛ ሳምንት የ ኢትዮጽያ ፕሪሜየር ሊግ ሲዳማ ቡና ፋሲል ከተማን አስተናግዶ በመጀመሪያ አጋማሽ ባስቆጠራቸው 3 ጎሎች ማሸነፍ ችለዋል።
በ4-3-3 አሰላለፍ ቅርፅ ሁለቱም ቡድኖች ይዘው ወደሜዳ ሲገቡ ፤ ገና ጨዋታው በተጀመረ 6ኛ ደቂቃ ሐብታሙ ገዛኝ ያሾልከለትን ኳስ ወንድሜነህ አይናለም አስቆጥሮ ሲዳማ ቡና 1-0 መምራት ሲችል ፋሲል ከተማዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ቢጥሩም የሲዳማ ተከላካይ መስመር ሰብረው ለመግባት ከብዷቸው ተስተውሏል፡፡ አዲስ ግዳይ ፣ሀብታሙ ገዛኝ እና ባዬ ገዛኝ የፊት መስመር እንቅስቃሴ ለ ፋሲል ተከላካዮች ፈተና ሆኖባቸው ውሏል።
በ 18ኛ ደቂቃ አዲስ ግደይ በግል ክህሎቱ ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ቀይሮ 2 ለ 0 እንዲመሩ አስችሏል፡፡

ከግቧ መቆጠረ በኃላ ተጭኖ በመጫወት ወደ ጎል መቅረብ የ ቻሉት የ አሌኮ ቡድን ሲዳማ ቡና ሲሆን በ 28ኛ ደቂቃ ወንድሜነህ አይናለም ከ መሃል ሜዳ አክርሮ በመምታት ግሩም ጎል በማስቆጠር ለራሱ 2ኛውን ለቡድኑ 3ኛ ግብ አስቆጥሯል።ሲዳማ ቡናዎች ሌላ ጎል ማስቆጠር የምችለውን ሳይጠሙ ቀርተዋል።3ለ0 መሪነት የመጀመርያ 45 ተጠናቆ ወደእረፈት አምርተዋል፡፡
ጎል ያልነበረው 2ኛ 45 ፋሲል ከተማ ግብ ለማስቆጠር የተጫዋች ቅያር ይስሀቅ መኩሪያን በ ፍፁም ከበደን እንዲሁም ፍሊፕ ዳውዝን በ ናትናኤል ጋንቹላ ቀይረው ብያስገቡም ጎል ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው በሲዳማ ቡና 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ -ሲዳማ ቡና
” በልጆቼ ተነሳሽነት አሸንፈናል ።አጥቂዎቼ ጥሩ ናቸው፡፡ከሜዳ ውጭም በማሸነፍ ወደ ፊት ለመምጣት ከልጆቼ ጋር እንጥራለን ።.”
አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ -ፋሲል ከተማ
” በጨዋታው የድካም ስሜት ነበረብን እሮብ ተጫውተን ዛሬ ስለ ተጫወትን ደክሞናል።መንገዱም እሚመች አይደለም።በጉዳት ላይ 3 ቁልፍ ተጫዋቾች ነበሩን፡፡”
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”5″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”0″ align=”none”]
አስተያየት ይስጡ