መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ሰበታ ላይ ሲዳማ ቡና ወሳኝ ድል አስመዝግቧል
ሪፖርትሲዳማ ቡናወልዲያየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ሰበታ ላይ ሲዳማ ቡና ወሳኝ ድል አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ወልዲያ ከተማ ሰበታ ላይ ሲዳማ ቡናን ባስተናገደበት ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከተማን 2-1 በመርታት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል፡፡

ዛሬ ሰበታ ላይ ወልዲያ ከተማን ከ ሲዳማ ቡና ያገናኘው ጨዋታ ወልዲያ ላይ በሼህ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲዬም መካሄድ ቢኖርበትም ፡የኢትዬጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ወልዲያ ከተማ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ለ1 ዓመት ከሜዳው 500ኪሜ ወጥቶ በፌዴረሬሽኑ በተመዘገበ ሜዳ እንዲጫዎት ባሰለፈው የቅጣት ውሳኔ ምክንያት ጨዋታው ሰበታ ላይ ሊካሄድ ችሏል፡፡

ልክ 8:05 ሲል በጀመረው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ወልዲያ ከተማ ባለፈው ሳምንት አዲስአበባ ላይ ከመቆለ ከተማ ጋር ያለ ግብ ነጥብ ከተጋሩበት የመጀመሪያ 11ተሰላፊዎች የ2 ተጨዋቾችን ለውጥ ሲያደርጉ አሳልፈውንና ያሬድን በኤዶምና አማረ በመተካት ሲገቡ በእንግዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች በኩል ባለፈው ሳምንት በሜዳቸው በጅማ አባጅፋር ሽንፈትን ካስተናገዱበት ስብስብ የ4 ተጨዋቾችን ለውጥ በማድረግ ፍቅሩ፡ወንድሜነህ፡አዲሱና፡ክፍሌን፡በማሳረፍ ዬናታን፡ወንድሜነህ፡መሳይና፡ፍፁምን፡በመተካት ገብተዋል፡፡

ለመጫዎት ምቹ ባልነበረው የሰበታ ሜዳ ሁለቱ ክለቦች ተመጣጣኝ እና ለተመልካች ማራኪ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ ለማሸነፍ በሁለቱም ክለቦች በኩል ገና ከመጀመሪያው ደቂቃ ከፍተኛ ጀምሮ ፍላጎት ነበር፡፡በጨዋታው ወደ ግብ በመድረስም በኩል ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ የነበረ ቢሆንም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በማድረግ ሲዳማዎች ቀዳሚ ነበሩ፡፡የሲዳማ ቡናው ወንድሜነህ አይናለም በ6ኛው ደቂቃ ብቻውን በቀኝ መስመር በኩል በመግባት ከወልዲያው ግብ ጠባቂ ቤሊንጋ ጋር ፊት ለፊት ቢገናኝም ሳይጠቀምበት ቤሊንጋ አውጥቶበታል፡፡በዚህም ወልዲያዎች ለተሞከረባቸው የግብ ሙከራ አጠፋውን ለመመለስ ባደረጉት ጥረት በ9ኛው ደቂቃ በመስፍን ኪዳኔ አማካኝነት ግብ ለማስቆጠር ባደረጉት ጥረት ኳስ በሲዳማ ቡና ተከላካዮች ተጨርፎ በመውጣቱ ባይጠቀሙበትም የመጀመሪያውን የማዕዘን ምት ማግኘት ችለው ነበር፡፡ጨዋታው ቀጥሎ በደቂቃዎች ልዩነት ሲዳማ ቡናዎች በ12ኛው ደቂቃ በግራ መስመር በኩል ፈቱዲን ጀማል ለፍፁም ተፈሪ ያቀበለውን ኳስ በድንቅ አጨራረስ ፍፁም ተፈሪ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡

ከግቧ መቆጠር በሇላ ብዙም ሳይቆዩ ሲዳማዎች በፍፁም ተፈሪ አማካኝነት ሌላ የግብ ሙከራ ሲያደርጉ፡ ወልዲያዎች በ17ኛው ደቂቃ አንዷለም ንጉሴ (አቤጋ) ጣጣውን ጨርሶ ለኤዶም የሰጠውን ኳስ ኤዶም ኳስን ከመረብ ጋር ያገናኛል ተብሎ ሲጠበቅ በግቡ አግዳሚ ወደ ላይ ኳስ በመውጣቷ አቻ የሚሆኑበትን ወርቃማ ዕድል አባክነዋል፡፡ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመድረስ የግብ ሙከራዎች በበዙበት በዚህ ጨዋታ በ20ኛው ደቂቃ ሲዳማ ቡናዎች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት በአጥቂው አዲስ ግደይ አማካኝነት ለግብ የቀረበ ሙከራ ሲያደርጉ፡ወልዲያ ከተማዎች በ23ኛው ደቂቃ በቀኝ መስመር በኩል በላይ አባይነህ ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ አንዷለም በግንባሩ በመግጨት ባደረገው የግብ ሙከራ ኳሷ በግቡ ቋሚ ስትወጣ ወልዲያዎች የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ለመመከት ያደረጉት የጨዋታ እንቅስቃሴ ውጤት ነበር፡፡

ወልዲያ ከተማዎች በ35ኛው ደቂቃ የአቻነት ግብ ለማግኘት ባደረጉት ጥረት አንዷለም ንጉሴ የሲዳማ ተከላካዬችን አታሎ አልፎ ወደ ሳጥን ሲገባ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ መሳይ አያኖ ግቡን ለቆ መውጣቱን የተመለከተው አቤጋ ኳሷን ወጋ(ቺፕ) በማድረግ በግብ ጠባቂው አናት ላይ በመላክ ወደ ግብ የላካት ኳስ ከመረብ ጋር ተገናኘች ሲባል የግቡን አግዳሚ ገጭታ ስትመለስ የሲዳማ ተከላካዮች እንደምንም ያወጡት ኳስ እንዳለመታደል ሁኖ ወልዲያዎች አቻ መሆን የሚችሉበት ዕድል ሲባክን በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ መገባደጃ ደቂቃ የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ ከወልዲያው ግብ ጠባቂ ቤሊንጋ ጋር ተገናኝቶ ያገኘውን ኳስ ሳይጠቀምበት የጨዋታው አጋማሽ ተጠናቆ ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ እንደተጀመረ ወልዲያዎች የአቻነት ግብ ለማግኘት ባደረጉት እንቅስቃሴ በ46ኛው ደቂቃ በበላይ አባይነህ አማካኝነት ለግብ የተቃረበ ሙከራ ሲያደርጉ ግባቸውን ላለማስደፈር ወደ ሇላ አፈግፍገው ሲጫዎቱ የቆዩት ሲዳማዎች በ55ኛው ደቂቃ የወንድሜነህ አይናለም የግል ብቃት ታግዘው ይሄው ተጨዋች ኳስና መረብን በማገናኘት ለራሱ የጨዋታውን የመጀመሪያ ግብ ለቡድኑ 2ኛ ግብ በማስቆጠር ሲዳማዎች ልዩነቱን ወደ 2 ማስፋት ችለዋል፡፡

ወልዲያ ከተማዎች ሁለተኛ ግብ ቢያስተናግዱም በነበራቸው ትልቅ ተነሳሽነት ወደ ፊት አጥቅተው በመጫዎት በ58ኛው ደቂቃ አንዷለም ንጉሴ ከሲዳማው ግብ ጠባቂ መሳይ በ4ሜትር ርቀት ወደ ግብ የመታው ኳስ ገባ ሲባል በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው መሳይ አያኖ ኳሱን መያዝ ችሏል፡፡ወልዲያዎች ከፍተኛ የማጥቃት ዘመቻ በማድረግ ላይ ባሉበት እንቅስቃሴ ከሳጥን ውጭ በ60ኛው ደቂቃ በላይ አባይነህ በግምት 24ሜትር አክሮ የመታት ኳስ ከመረብ ጋር ተገናኝታ ወልዲያዎችን የበለጠ ወደ ጨዋማው የመለሰች ግብ ሁና ተመዝግባለች፡፡

ከግቧ መቆጠር በሇላ ሲዳማ ቡናዎች ሌላ ግብ ላለማስተናገድ የበለጠ ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ሇላ ተመልሰው በመስመር በኩል በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማግኘት ሲጫዎቱ ሌላ ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው መጫዎት የቻሉት ወልዲያዎች በ71ኛው ደቂቃ ግብ ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጭ በሚል ግቧ ስትሻር፡ወልዲያዎች በቀኝ መስመር በኩል በ85ኛው ደቂቃ አቻ መሆን የሚችሉበትን አጋጣሚ በላይ አባይነህ ከሲዳማው ግብ ጠባቂ ጋር ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ሲባክን በ86ኛው ደቂቃ አጥቂው ኤዶም በግራ መስመር በኩል ሰብሮ በመግባት ድንቅ ጎል ሲያስቆጥር የመስመር ዳኛው ኤዶም ከጨዋታ ውጭ ነው በሚል ግቧ ስትሻር በስታዲየም የነበረው ደጋፊ በዳኞች ላይ በከፍተኛ ድምፅ ተቃውሞ ከማሰማቱ ባሻገር ከተቃራኒ ደጋፊዎች ጋር በተፈጠረ ብጥብጥ ጨዋታው ለ10 ደቂቃዎች ያህል የተቋረጠ ሲሆን የፀጥታ አስከባሪ አካላት ብጥብጡን ለማብረድና ወደ ነበረበት ለመመለስ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ካታንጋና ዳፍትራክ የታደመውን ተመልካች ሙሉ በሙሉ ስታዲዬሙን ለቆ እንዲዎጣ በማድረግ ጨዋታውን ወደ ነበረበት መመለስ ተችሏል፡፡

ከክስተቱ ማብቂያ በሇላ ጨዋታው ካቆመበት 86ኛው ደቂቃ ሲቀጥል በዚሁ ደቂቃ ወልዲያዎች በቀኝ መስመር በኩል ኤዶም ያሻገረውን ኳስ ብርሃኔና ሸዋለም ማግባት የሚችሉትን ኳስ በመዘናጋታቸው ወርቃማ አጋጣሚ ሲያመልጣቸው በ87ኛው ደቂቃ ኤዶም በረጅሙ ያሻገረውን ብርሃኔ በጭንቅላቱ ገጭቶ አስቆጠረው ሲባል የግቡ ቋሚ መልሶበታል፡፡በሲዳማ ቡናዎች በኩል ምናልባትም ልዩነቱን ያሰፉበታል የተባለ የግብ ሙከራ መሀመድ ያቀበውን ኳስ ፍፁም ሞክሮት ቤሊንጋ ሲያመክንበት ጨዋታው 90ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ በ86ኛው ደቂቃ ባዬ በጉዳት ከሜዳ ለህክምና እንደወጣ ሌላ ተጨዋች ቀይሮት የገባ ቢሆንም ባዬ ተመልሶ ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን ከደጋፊዎች በሰማው ጩኸት ኳስ ሳይነካ ወዲያውኑ በካታንጋ በኩል ሲወጣ ወልዲያዎች 12ኛ ተጨዋች ነው በሚል ክስቢ ያስመዘግቡም ጨዋታው በሲዳማ ቡና 2-1አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ በሁለቱም በኩል የደረጃ ለውጥ ሳይኖር ሲዳማዎች በ24 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ባሉበት 11ኛ ላይ ሲቀመጡ ወልዲያዎች በ20 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...