መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ​ሪፖርት | መቐለ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
መቐለ ከተማሪፖርትአዳማ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​ሪፖርት | መቐለ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

አጋራ
አጋራ

 

በ8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አዳማ ከተማን ያስተናገዱት መቐለ ከተማዎች 1-1  በሆነ ውጤት ተለያይተዋል ።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ  መቐለ ከተማ ጥሩ መንቀሳቀስ  ሲችሉ የማግባት እድሎችን ፈጥረው ሳይጠቀምቧቸው ቀርቷል።
ከእረፍት በፊት በ34ኛናበ36ኛው ደቂቃዎች እንዳለ ከበደ የሞከራቸው ሁለት ኳሶች የግቡ ቋሚ መልሶበታል።
በአንፃሩ አዳማ ከተማ አጥቂዎች በመጀሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ጥሩ ግብ መሆን የሚችሉ ኳሶችን ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

ከእረፍት መልስ በ52ኛው ደቂቃ ላይ መቐለ ከተማ  ፍፁም ቅጣት በማግኘቱ አማኑኤል ገብረሚካኤል  በመታት  ቡድኑን  መሪ ማድረግ ችሏል።

አዳማ ከተማዎች ከጎልዋ መቆጠር በኃላ ጫና ፈጥረው መጫወት ችለዋል፡፡ የመቐለ ከተማ ደጋፊዎች ደስታቸውን በገለጹ በአምስት ደቂቃ ልዩነት የአዳማ ከተማዎች ያገኙዋትን ቅጣት ምት ዳዋ ሁቴሳ  በግሩም ሁኔታ አክርሮ በመምታት ቡድንን ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስቸሎታል።
የአሰልጣኞች አስተያየት 

 አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ-መቀለ ከተማ

“በጨዋታው ጥሩ ተንቀሳቅሰናል አጥቅተን ለመጫወት ችለናል ሆኖም ያገኘናቸውን የጎል ማግባት አጋጣሚዎች ሳንጠቀም መቅረታችን ዋጋ አስከፍሎናል፡፡”

 

አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽ -አዳማ ከተማ

“በመጀመሪያው አጋማሽ ተበልጠን ነበር፡፡በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ቅርፃችንን በመቀየር ተቀናጅተን ለመጫወት በመቻላችን ነጥብ ተጋርተን ልንወጣ ችለናል፡፡ የመቐለ ከተማ ደጋፊዎች ከገባን ጀምሮ ያደረጉልን አቀባበል በጣም አስደስቶናል፡፡ ልናመሰግናቸውም እንፈልጋለን፡፡”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...