ሙሉጌታ ምህረት ሀዋሳ ከተማን ተረክቧል !

 

ከአዲሴ ካሳ ጋር የተለያዩት ሀዋሳ ከተማዎች የቀድሞው ተጫዋቻቸው ሙሉጌታ ምህረት የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ ሾመዋል ::

ሙሉጌታ ምህረት ሀዋሳ ከተማን እየመራ ቀጣዮቹን አንድ አመት ከስድስት ወር የሚያቆየውን ኮንትራት መፈራረሙን ለማወቅ ተችሏል ::

ሙሉጌታ ምህረት ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ቤት የውበቱ አባተ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግል ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ በዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ የኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ማገልገሉ የሚታወስ ነው ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor