መከላከያ ዮርዳኖስ አባይን ምክትል ተደርጎ ሊሾም ነው

 

መከላከያ ለ2013 የውድድር አመት አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌን አሰልጣኙ አድርጎ በይፋ ቀጥሯል፡፡ የአሠልጣኙ ወኪልና ክለቡ ከፍተኛ ድርድር አድርገው መስማማታቸው ታውቋል፡፡ አሁን ደግሞ በአሠልጣኙ የሚፈለገውን ዮርዳኖስ አባይን ምክትል አድርጎ ለመቅጠር ሃላፊዎቹ ከዮርዳኖስ ጋር ነገ ለድርድር ይቀመጡና በ48 ሰአት ውስጥ የዮርዳኖስ ሹመት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ክለቡ ኮንትራት ከነበረው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው/ሞውሪንሆ/ ጋር በመነጋገር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል፡፡ የክለቡ አመራሮች ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያሳልፈናል በሚል አሰልጣኝ ዮሐንስ ላይ ተስፋ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport