መቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች አስፈርሟል !
ሀትሪክ ስፖርት በጭምጭምታ አምዱ እንዳስነበባችሁ በጣናው ሞገድ ድንቅ የሚባል የውድድር ዓመትን ማሳለፍ የቻለው ፍጹም አለሙ ማረፊያውን መቐለ 70 እንደርታ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል ።
ፍጹም ዓለሙ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጎልተው መውጣት ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል ውስጥ አንዱ የሆነው ፍጹም በመቐለ ቤት ለሁለት ዓመታት እንደሚቆይ ተጠቁሟል ።
ፍጹም ዓለሙ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተቋረጠው ፕርሚየር ሊግ ዘጠኝ ጎሎችን በማስቆጠር በኮከብ አግቢነቱ ፍክክር ላይ ይገኝ ነበር ።