ሎዛ አበራ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጣለች !
የሉሲዎቹ እና የማልታው ሻምፒዮን ክለብ ቢሪኪርካራ ክለብ የፊት መስመር አጥቂ ሎዛ አበራ ድንቅ የውድድር ዓመትን ማሳለፏ የሚታወስ ነው ።
ትላንት ምሽት የማልታ እግር ኳስ የተጫዋቾች ማህበር ባካሄደው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ምርጫ ላይ ሎዛ አበራ ማሸነፏ ተገልጿል ።
ሎዛ አበራ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች በመባል የሀገሪቱ እግር ተጫዋቾች ማህበር መምረጡን ይፋ አድርጓል ።