ሎዛ አበራ ሀትሪክ ሰርታለች

 

ሎዛ አበራ ዛሬ ምሽት በማልታ የሴቶች ሊግ ቢሪኪርካራ ሞስታን አስተናግዶ 9-0 ሲያሸንፍ። ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችላለች።

ንግስቷ አሁንም ማምረቷን ተያይዛዋለች። ተከላካዮችን እያጋደመች ኳስ እና መረብን በማገናኘት አሁንም እየነገሰች ነው። ተጫዋቿ ሞስታ ላይ ያስቆጠረችው ግብ በአጠቃላይ ወደ 26 ከፍ ያደረገችበትን ግብ ነው ያስመዘገበችው። 30,58 እና 89ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረችው። በአጠቃላይ በማልታ ቆይታዋ ደግሞ 30 ግቦችን ማስቆጠር ችላለች።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor