ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሲሰጥ የነበረው የተጫዋቾች ምዝገባ የመረጃ አያያዝ ስልጠና በትናትናው እለት ተጠናቀቀ፡፡

የአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ባዘጋጀው /FIFA Connect Platform/ የመረጃ ቋት ተጫዋቾችንና የክለብ አባላትን መረጃ አያያዝ ስልጠና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለሁለት ቀን ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በትናንትናው እለት 05/06/2011 ዓ/ም ተጠናቀቀ፡፡

ለሁሉም ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በተዘጋጀው ስልጠና አስራ አንድ ክለቦች የተገኙ ሲሆን በስልጠናው ላይ በአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ባዘጋጀው /FIFA Connect Platform/ የመረጃ ቋት አስተማማኝ እና የተሟላ የተጫዋቾች እና የቡድኑ አባላትን ምዝገባ መረጃን መያዝ የሚያስችል ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ይህ ለውጥ የተጫዋቾች ዝውውር ግልፅነት እና ፕሮፌሽናሊዝምን ከመጨመር ባሻገር በተለይ ውጤታማ እና ወጥ የሆነ የተጫዋቾች የልምምድ ካሳ ክፍያ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል ፕሮግራምሙም ከሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

በመጨረሻም በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀ ሰርተፊኬት ሥልጠናውን ለተከታተሉ ሰልጣኞች ተበርክቶላቸዋል፡፡

via – EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor