መነሻ ገጽ ዜናዎች ለአለም ብርሀኑ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆነ
ዜናዎች

ለአለም ብርሀኑ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆነ

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ህዳር 6 አንታናናሪቮ ላይ
ከማዳጋስካር እና ህዳር 9 መቐለ ላይ ከአይቮሪኮስት ጋር ላለበት 2021
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅቱን ሰኞ ጥቅምት 24/2012ዓ.ም
ማረፊያውን አክሱም ሆቴል መቐለ በማድረግ ይጀምራል።
የብሄራዊ ቡድኑ አባላትም እሁድ ጥቅምት 23/2012ዓ.ም በሸበሌ
ሆቴል ከቀኑ 9 ሰዓት ሪፖርት በማድረግ ሰኞ ከረፋዱ 5ሰዓት ወደ
መቐለ ያቀናሉ።
በመቐለ ቆይታቸው በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ የሚሰሩ ሲሆን ህዳር 1
ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ህዳር 2/2012ዓ.ም የቡድኑ አባላት ወደ
ማዳጋስካር የሚያመሩ ይሆናል። ህዳር 6 ጨዋታቸውን በማዳጋስካር
ካካሄዱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ህዳር 7 ወደ አዲስ አበባ በመለስ፤ ህዳር 8
ወደ መቐለ በመሄድ ህዳር 9 ከቀኑ 10 ሰዓት ከአይቮርኮስት ጋር
የሚጫወቱ ይሆናል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነው
ለዓለም ብርሃኑ ከክለቡ ጋር በቅድመ ዝግጀት ልምምድ ላይ በደረሰበት
ጉዳት ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ መሆኑ ታውቋል። በምትኩ የመከላከያ
እግር ኳስ ክለብ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ ጥሪ ተደርጎለታል።

ምንጭ ኢእፌ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...