“ለሲዳማ ቡና ውሌን ያራዘምኩት ክለቡ ስለተመቸኝ ነው” ዳዊት ተፈራ /አዚል/ /ሲዳማ ቡና/

 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሲዳማ ቡናን የአማካይ ክፍል በስኬታማነት ከሚመሩት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ ዳግመኛ ለክለቡ ለመጫወት ውሉን አራዝሟል፤ የሲዳማው አማካይ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ጥሩ ብቃት ያለው ተጨዋች ሲሆን ይህን ተጨዋች ከክለቡ ጋር ዳግም ስለመቀጠሉና ሌሎችን ጉዳይ አንስተንለት ምላሽ ሰጥቶናል፡፡

ሀትሪክ፡- በሲዳማ ቡና የነበረህ የተጨዋችነት ቆይታህ በጣም ጣፋጭ ነበር?

ዳዊት፡- አዎን፤ ለቡድኑ ለሁለት ዓመታት ያህል ተጫውቻለው፤ ቆይታዬንም በጣም ነው የወደድኩት፤ ጥሩ ቡድን ነበረንና መልካም የሚባል ጊዜያቶችን ነው ያሳለፍኩት፡፡

ሀትሪክ፡- የሲዳማ ቡና ቆይታ ላይ ለአንተ ጥሩ የሚባሉት ጊዜያቶችህ የትኞቹ ናቸው?

ዳዊት፡- በ2011 ያሳለፍነው የውድድር ጊዜ ለእኔ የተለየ እና በጣምም ጥሩ የነበረ ነው፤ ያኔ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሣት ከጫፍም ደርሰን ነበርና ምንም እንኳን ዋንጫውን ብናጣም ምርጥ የውድድር ጊዜን ያሳለፍንበት ወቀት ስለነበር ያን ጊዜ ፈፅሞ አልረሳውም፡፡

ሀትሪክ፡- በክለቡ ቆይታህ የተቆጨህበት ጊዜስ?

ዳዊት፡- አሁንም ያንን ጊዜ እጠቅስልሃለው፤ ዋንጫ ማጣታችን ይቆጨኛል፤ ከዛ ውጪም ለብሔራዊ ቡድናችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተመረጥኩበት አመት ላይም ከቪድ 19 ወደ አገራችን ገብቶ የአፍሪካ ዋንጫው ውድድሮቹ በመሰረዛቸው ያስቆጨኛል፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ይህ ወረርሽኝ በሀገሪቱ ላይ የተከሰተ ስለሆነም ምንም ነገርን ማድረግ አይቻልም፡፡

ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ተጨዋች ሆነህ ነበር፤ አሁንስ በዛ ስብስብ ውስጥ ነው የምትገኘው?

ዳዊት፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በያዘበት ሰዓት እኔ ለዋልያዎቹ መመረጤ ተነግሮኝ ነበር፤ ያኔ ስመረጥም አሰልጣኙ አሁን የጠራሁክ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያው ውድድር በየአራት ቀኑ የሚደረግ ስለሆነ ውድድሩም ቶሎ ቶሎ የሚከናወን ስለሆነ ቅድሚያ የምስጠው ለሲኒየር ተጨዋቾች ነው፤ እናንተን እንደ አዲስ ስለጠራዋችሁ የቡድኑ አባል ሆናችሁ ትቀያላችሁ ብሎን ነበርና ይሄን ነው የማውቀው፤ ያም ሆነ ይህ ለቀጣይ ብሔራዊ ቡድን ብኖርም ባልኖርም በድጋሚ ለብሔራዊ ቡድን ለመጠራት ከፍተኛ ጥረትን አደርጋለው፡፡

ሀትሪክ፡- በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ ውልህን አራዝመሃል..?

ዳዊት፡- በሚገባ! ምክንያቱም ክለቡ ለእኔ ጥሩ እና በጣም የተሰማማኝ ነው ስለዚህም፤ ለዛም ነው እዚ ቡድን ውስጥ ውሌን ላራዝም የቻልኩት፡፡

ሀትሪክ፡- በመከላከያ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ስትጫወት ብዙዎቹ ያውቁ ነበር ከዛ ጊዜ አንስተህ በኳሱ ጥሩ ለውጦችን እያሳየህ ነው?

ዳዊት፡- አዎን፤ መጀመሪያ ለመከላከያ ተስፋ ቡድን ነው የተጫወትኩት፤ ከዛም ወደ ጅማ አባጅፋር በብሔራዊ ሊግ ተጫወትኩና ወደ ሱፐር ሊግ ቡድኑን ካስገቡት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆንኩ፤ በመቀጠልም ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲገባም ድርሻዬን አበረከትኩ፤ ለወጣት ብሄራዊ ቡድንም ተመርጬ ለመጫወት ቻልኩ፤ ሲዳማ ቡናም ገብቼ የተሳካ ጊዜን አሳለፍኩ፤ ስለዚህም አሁን የምገኝበትን ደረጃ ሳየው ራሴን እያሻሻልኩ ነው የምገኘው፡፡

ሀትሪክ፡- ሲዳማ ቡናን አዲስ ግደይ ለቋል?

ዳዊት፡- ቢኖርልን ጥሩ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን እሱ የተሻለ ነገርን ስላገኘ ቡድኑን ለቋል፤ ያም ሆኖ ግን ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ስለመጡልን በመጪው ዓመትም ለዋንጫ የምንፎካከር ይሆናል፡፡

ሀትሪክ፡- በመጨረሻ……?

ዳዊት፡- ኮሮና ቫይረስን ፈጣሪ ያጥፋልን፤

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website