በተመስገን ዳና እየተመሩ በወቅቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ላይ ዘግይተው በመግባት በንቃት አየተሳተፋ ሚገኙት ደቡብ ፖሊሶች ሃይማኖት ወርቁን ከወላይታ ዲቻ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።በ2010 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወላይታ ዲቻ የተሳካ ውድድር ሲያሳልፍ የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች የነበረው ሃይማኖት አምና ከፕሪምየር ሊጉ የወረደውን ደቡብ ፖሊስን በሚቀጥሉት ቀናት ይቀላቀላል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከወላይታ ድቻ ጋር ያሳለፈው የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ፣ሀዋሳ ከተማ፣ጅማ አባጅፋር ተጨዋች ሃይማኖት አንደ አዲስ አየተገነባ ያለውን ደቡብ ፖሊስን በይፋ ሲቀላቀል የተመስገን ዳና የክረምቱ ፈራሚዎች ቁጥርን ወደ 15 ከፍ ያደርገዋል።
አስተያየት ይስጡ