የኢትዮጵያ እና ካፍ ግንኙነት አሁንም ቀጥሏል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮሚቴዎች እና የካፍ የሚዲያ ባለሙያ እጩዎች ዝርዝር በአሁን ሰዓት በካፍ ይፋ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁለት ክፍሎች ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ፕረዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀል እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንደምትወከል በዝርዝሩ ውስጥ መካተት የቻሉ ብቸኞቹ አባላት ናቸው ፡፡
በዚህም መሰረት በአፍሪካ ብሔራዊ ሻምፒዮና ኮሚቴ ውስጥ አቶ ኢሳያስ ጅራ በአባልነት ከተካተቱት 25 አባላት አንዱ መሆን ሲችሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ አብነት ገ/መስቀል የክለቦች ፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት እና የክለቦች ውድድር አስተዳደር ኮሚቴ አባል በመሆነ ከተመረጡት 17 አባላት መካከል አንዱ መሆን ችለዋል ፡፡


አስተያየት ይስጡ