ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ አሰልጣኞች ለጎዳና ተዳዳሪዎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችን ሊያሰባስቡ ነው

 

በሀዋሳ ከተማ ከፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች ጀምሮ እስከ ፕሮጀክት አሰልጣኞች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚያስችል ቁሳቁሶችን ነው ከነገ ጀምረው የሚያከናውኑት።

አሰልጣኞቹ በዋነኝነት ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና አቅመ ደካሞ ለምግብነት እና ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ሂደት እንደሚያደርጉ ዛሬ ሀዋሳ ማውንቴን ሆቴል ላይ በነበራቸው ስብሰባ ገልፀዋል። የበኩሉን ድርሻ መወጣች የሚፈልግ ማንኛውም አካል መርዳት እንደሚችልም ተጠቁሟል። የቁሳቁስ መሰብሰብ ሂደት ከነገ ጀምር እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ያሉትን ሁሉንም መረጃ እየተከታተልን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።