መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ሪፖርት | ሀዋሳ ከተማ ቅዱስጊዮርጊስን በሙሉ የጨዋታ ብልጫ 4-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል
ሀዋሳ ከተማሪፖርትቅዱስ ጊዮርጊስየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ሀዋሳ ከተማ ቅዱስጊዮርጊስን በሙሉ የጨዋታ ብልጫ 4-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል

አጋራ
አጋራ

በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ሐዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮጊስ  አገናኝቶ በባለሜዳዮቹ ከሙሉ ጨዋታ ጋር 4ለ1 በማሸነፍ ነጥቡን 18 ማድረስ ችሏል።
   ባለሜዳዎቹ የበላይነት በታየበት ጫወታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ለግብ የቀረበ ሙከራ አልትመልክትንም ሆኖም ኳስን መስርተው በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ በመድረስ ጫና በመፍጠር ተጫውተዋል።በ14 ደቂቃ የተገኘውን ቅጣት ምት ሙሉአለም  ረጋሳ ለፍሬው ሰለሞን አሻግሮለት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።በቀኝ መስመር በኩል አዲስአለም ተስፍዪ ከታፈሰ ሰለሞን የተቀበለውን ኳስ አሻምቶት ሳይጠቀሙበት ቀርቷል።

በ18 ደቂቃ እስራኤል እሸቱ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የትሰጠውን ቅጣት ምት አዲስ ተስፍዪ መቶት የቅዱስ ጊዮጊሱ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኡዱካራ ወደ ውጪ አውጥቶታል።ከ3 ጨዋታ  ቅጣት በኃላ  የተመለሰው ፍሬው ሰለሞን ፍቅረየሱስ ተ/ማርያም እና ታፈሰ ሰለሞን መሐል  ሜዳውን ብልጫ በመውሰድ ጫና ፈጥረዋል።

በ36ተኛው ደቂቃ አዲስአለም ተስፋዪ ከቀኝ መስመር ያሻገረለትን ኳስ እስራኤል እሸቱ ተቀልብሶ መቷት ወደ ውጪ ስትወጣበት : በጨዋታው ብልጫ የተወሰደባቸው ፈረሰኞቹ ወደ መከላከሉ አመዝነው በመልሶ ማጥቃት በመጫወት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ  ጥፋት ተሰርቶባቸው ከቅርብ ርቀት ላይ የተገኘውን ቅጣትምት አበባው ቡጣቆ አክርሮ መቶት ግብ ጠባቂው ሳሆሆ ሜንሳ በግሩም ሁኔታ አምክኗታል።

በ39ኛው ደቂቃ ሙላለም ረጋሳ ከግብ ክልል ውጪ አክርሮ የመታትን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲያደናት ከ3 ደቂቃ በኃላ ፍሬው ሰለሞን ከአዲስአለም ተስፋዪ የተቀበለውን ኳስ ወደ ግብ ቀይሮት ባለሜዳዎቹን መሪ አድርጓቸው ውደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

በሁለተኛ አጋማሽ በይበልጥ ተጠናክረው የገቡት ሐዋሳ ከተማዎች ጫና ፈጥረው ተጫዉተዋል።በ56ተኛው ደቂቃ ላይ ፍሬው ሰለሞን ከርቅት ያሻገረውን ኳስ ታፈሰ ሰለሞን ተከላካዮችን እና ግብ ጠባቂውን አታሎ ከመረብ አሳርፏት ጎሉን 2ለ0 ቀይሮታል።

በ62ተኛው ደቂቃ   የቅዱስ ጊዮጊሱ ግብ ጠባቂው ሮበርት ኦዶካራ በጉዳት ከሜዳ ለመውጣት ሲገደድ እሱን በመተካት ዘሪሁን ታደለ ወደ ሜዳ ገብቷል።

በ82ተኛው ደቂቃ ፍሬው ሰለሞን ከታፈሰ ሰለሞን  የተቀበለውን  ኳስ አሻምቶት እስራኤል እሸቱ በጭንቅላት አስቆጥሮ  3ለ0 አድርጎታል።የጨዋታውን የበላይነት የተቆጣጠሩት ባለሜዳዎቹ ተጭነው በመጫወት ከቀኝ መስመር አዲስ አለም ተስፋዪ ያሻገረውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን አረጋግቶ ለታፈሰ ሰለሞን አቀብሎት ወደ ግብ ቀይሯታል ጫዎታ 4ለ0 ሆኗል።

ለፈረሰኞቹ ብቸኛዋን ጎል ያስቆጠረው  ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ሰይዴ ኬታ ሲሆን   ጨዋታውም  4ለ1 በሆነ ውጤት በባለሜዳውቹ ሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
የአሰልጣኞች አስተያየት

 አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ~ ሀዋሳ ከተማ

በዛሬው ጨዋታ ጥሩ ነበርን። በጨዋታው  በሁለተኛው አጋማሽ ጉድለታችንን ማስተካከል  መቻላችን በጥሩ ጉን ሊወሰድ ይችላል። በማጥቃቱ ረገድ ያለፉት ጨዋታወች ላይ ከፍተኛ ክፍተት ነበረብን። ይህ ችግር ዛሬ ተፈቷል ብዬ ባላስብም በተወሰነ መልኩ ቀርፈናል ማለት እችላለሁ። ባለፉትን ተከታታይ ጨዋታዎች ፍሬውን በቅጣት አላገኘነውም ነበር። ዛሬ ማግኘታችን ይበልጥ አጠንክሮናል። ዛሬም በርካታ ተጫዋቾትን በጉዳት ሳንይዝ ብንገባም በጥሩ እንቅስቃሴ አሸንፈን ወጥተናል፡፡

ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ ~ ቅዱስ ጊዮርጊስ

በቅድሚያ ሀዋሳ ከተማዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ዛሬ ሀዋሳዎች ያሳዩት ብቃት ጥሩ ነበር። በሙሉ ደቂቃውም የተሻሉ ነበሩ ማለት ይቻላል። ነገር ግን በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ እንደልብ እንዲጫወቱ ሰፊ ክፍተት መስጠታችን የጎዳን ይመስለኛል። የሀዋሳ ከተማ ተጫዋቾች የሚያደርጉትን ፈጣን እንቅስቃሴ ተጫዋቾቼ ለማስቆም ያደረጉት ጥረት ዝቅተኛ ነበር። ዛሬ በአጠቃላይ ጥሩ አልነበርንም። በሁለተኛው የሊጉ ዙር ግን የተጎዱ ተጫዋቾች ሲመለሱ ጥሩ ቡድን ይዘን እንደምንቀርብ ሙሉ እምነት አለኝ። በቡድኔም ልጆች ሁሌም ደስተኛ ነኝ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...