ሀትሪክ 14ኛ ሳምንት| ፕሪምየር ሊግ ክስተቶች

👉👉በርካታ ካርዶች የተመዘዙበት ጨዋታ

👉👉አጨቃጫቂ የነበረው ፍፁም ቅጣት ምት

👉👉በተጫዋቾች ቅያሪ ላይ ጣልቃ የገቡት የፀጥታ ሀይል

👉👉ለወላይታ ድቻ ሶስት ነጥብ ያሰገኘችው የአሰልጣኙ ለውጥ

👉👉በቀይ ካርድ የተሰናበተት ሽመክት እና ደስታ

👉👉ወደ ግርማ ሞገሱ የተመለሰው ኦኪኪ ኦፎላቢ

በ14ኛ ሳምንት የተመለከትናቸው ልየት ያሉ ነገሮች እንደሚከተለው አቅርበንላቹሀል።

በርካታ ካርዶች የተመዘዙበት ጨዋታ

በዚህ ሳምንት በአንድ ጨዋታ ብቻ 11 የማስጠንቀቂያ ካርዶች ሲመዘዙ ለመጀመሪያ ግዜ ሲሆን። ይህም በአዲስ አበባ ስታዲዮም ሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው 0-0 በሆነ አቻ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ የተመዘገበ ነው። የጨዋታው ዋና ዳኛ ባህሩ ተካ ውሳኔዎች ላይ የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች ተቃውሞን በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ተስተውለዋል ::

አጨቃጫቂ የነበረው ፍፁም ቅጣት ምት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 እየመራ ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ ተብሎ ሲጠበቅ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሄኖክ አዱኛ ሱራፌል ዳኛቸው ላይ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የእለቱ አርቢትር የፍፁም ቅጣት ምት ይሰጣሉ። ሆኖም ግነ አንዳንድ የቅዱስ ጊዮርጊስ የዳኛዋን ውሳኔ ለመቀበል ተቸግረው ታይተዋሎ። ከዚህ ባለፈም አላስፈላጊ ንትርክ እና ጭቅጭቅ ውስጥ ሲገቡም ታይተዋል። ይህ መታረም ያስፈልገዋል።

በተጫዋቾች ቅያሪ ላይ ጣልቃ የገቡት የፀጥታ ሀይል

በሳምንቱ አስገራሚ ከነበሩ ጉዳይ አንዱ ሰበታ ከተማ የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና የተጫዋች ለውጥ በሚያደርጉበት ወቅት የፀጥታ ሀይሎች ቅያሪውን ለማዘግየት ወደ አሰልጣኞች ቦታ የሄዱበት መንገድ እና ቅያሪው ለተወሰኑ ደቂቃዎች የዘገየበት መንገድ መነጋገሪያ ነበር።

ለወላይታ ድቻ ሶስት ነጥብ ያሰገኘችው የአሰልጣኙ ለውጥ

በሜዳው ባህርዳርን አስተናግዶ 1-0 ያሸነፈው ወላይታ ድቻ። አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ ያልተጠበቀ ለውጥ አድርገው የሶስት ነጥብ ማግኛ መንገድ ሆኖላቸዋል። በጨዋታው በጣም ደካማ እንቅስቃሴ ያደረጉት ወላይታ ድቻዎች ወደግብ የመድረስ ደካማ አጋጣሚ ቢኖራቸውም የመሀል ተከላካዩ ደጉ ደበበን በፊት አጥቂ መስመሩ ባየ ገዛኸኝ ቀይረው በማስገባት ተሳክቶላቸው ባየ ገዛኸኝ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።

በቀይ ካርድ የተሰናበቱት ሽመክት እና ደስታ

የፋሲል ከነማው ሽመክት ጉግሳ እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ደስታ ደሙ በፈጠሩት አለመግባባት ምክንያት በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሊወገዱ ችለዋል። ሁለቱም ተጫዋቾች የኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰን ውሳኔ ላለመቀበል ሲቃጣቸው ተስተውሏል።

ወደ ግርማ ሞገሱ የተመለሰው ኦኪኪ ኦፎላቢ

በክረምቱ መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ ከቡድኑ ጋር ለመቀናጀት ተቸግሮ የነበረው ግዙፋ ናይጀርያዊ አጥቂ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻልን አሳይቶ በዚህኛው ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ላይ ሀትሪክ መስራት ችሏል።ከሌሎች የቡድን አጋሮቹ ጋር ጥሩ ቅንጅት እየፈጠረ ሚገኘው ኦኪኪ በዚህ ውድድር ዓመት ያስቆጠራቸው ግቦች ወደ 6 ከፍ ማድረግ ችሏል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor