በበዓል ምክንያት በመደበኛ ቀንዋ ለንባብ ያልበቃችው ሀትሪክ ነገ (ረቡዕ) እንደተለመደው የአንባቢያንን ቀልብ የሚስቡ ልዩ ጥንቅሮቿ አንባቢዎቿ እጅ ትደርሳለች
ሀትሪክ በነገው ዕትሟ፦ በአቀራረቡና በይዘቱ ለየት ባለውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባገኘው The Big Interview ዓምዷ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የማይዘነጋ ደማቅ አሻራውን ያሳረፈው ግን ደግሞ በጉዳት ምክንያት ረዘም ላሉ ወራቶች ከውድድር ርቆ የነበረው የኢትዮጵያና የቅዱስ ጊዮርጊሱ የጎል ሠው የሆነው ሳላህዲን ሠይድ ከረዥም ጊዜ ዝምታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉዳቱ፣ በግልና በእግር ኳስ ህይወቱ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በተለይ ለሀትሪክ (exclusive) መሳጭ ቃለ-ምልልስ አድርጓል፤ሊያመልጦት የማይገባ ቃለ-ምልልስ ነውና የነገ ማለዳ ሀትሪክን ይጠብቁ!
ከዚህ በተጨማሪ ሀትሪክ በነገው እትሟ እንደተለመደው ወቅታዊና አዳዲስ ዜናዎችን እንዲሁም ቃለ-ምልልሶችን በሀገር ውስጥ ዘገባዎቿ ያካተተች ሲሆን በባህር ማዶ ዘገባዎቿ ደግሞ የማን. ዩናይትዱ የኦሌ ጉነር ሶልሻየር፣ የዩናይ ኤምሬ፣ ማን ሲቲ በሊቨርፑል ላይ ስለተቀዳጀው ድል እና ሌሎች በርካታ አዳዲስ እና ትኩስ ዘገባዎች ተካተዋልና የነገ እትም ሀትሪክ ጋዜጣዎ እንዳታመልጦ፡
የመጀመሪያ ባለ ቀለም ከሆነችው ሀትሪክ ጋዜጣ በተጨማሪ ድረ-ገፃችን ላይ ወቅታዊና ትኩስ ዜናዎች፣ አዳዲስ ቃለ-ምልልሶች፣ የጨዋታ ሪፖርቶችና የቀጥታ የጨዋታ ውጤቶችን ያገኛሉና አሁኑኑ የሀትሪክ ድረ-ገፅ (hatricksport.com) ቤተሰብ ይሁኑ፡
የሀትሪክ ስፖርት የነገው እትም የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ