ሀትሪክ በነገው እትሟ በኢትዮጵያ ቡና ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ደምቆ እያበራ የሚገኘውን አንፀባራቂው ኮከብ (The Rising Star) አቡበከር ናስርን በሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፊ ቃለ-ምልልስ በማድረግ ልታስኮመኩሞ መሰናዶዋን አጠናቃለች፡፡
አቡበከር ከሀትሪክ ጋር በነበረው እና በአንባቢዎቿ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈችበት በመጣችው The Big Interview አምዷ ከተጨዋቹ ጋር ያልተሰሙ እና ያልተነበቡ አነጋጋሪና አስደማሚ ብስለት የተሞላባት ቃለ- ምልልስ አድርጓል፤ ለመሆኑ አቡበከር ምን ብሎ ይሆን? አቡበከር ለኢትዮጵያ ቡና ስላለው ፍቅር፣ በኢትዮጵያ ቡና ማሳካት ስለሚፈልገው፣ ስለ ግል ህይወቱ፣ በፍቅር ጉዳይ ሳይቀር በማናገር ሀትሪክ ለታዳጊ ተጨዋቾችም ያላትን ክብር ያሳየችበት ቆይታ አድርጋለችና የነገ እትም እንዳያመልጦ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን አስመልክቶ የቅ/ጊዮርጊሱን አማካይ ታደለ መንገሻ እና የኢትዮጵያ ቡናውን ኢያሱ ታምሩንም አናግራ ተጨዋቾቹ ምላሽን ሰጥተዋል፤ ሀትሪክ ሌሎች መረጃዎችም አሏትና ያንብቧት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ለማን. ዩናይትድ አሸናፊነት ትልቅ ሚና የተጫወተውን ዴቪድ ዴሂያ ዙሪያ “ከግብ ጠባቂም በላይ” በማለት ልዩ ዘገባ ያቀረበች ሲሆን በአርሰናል፣ በቸልሲ፣ በሊቨርፑል እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎችን አካታለችና ነገ ማለዳ ይጠብቁን፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
#_አቡኪን
ለማንበብ ቸኩያለሁ
ይነጋልዎይ ነው የኔ ጥያቄ?