መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ጋዜጣዎ ሳምንቷን ጠብቃ ከእጅዎ ልትደርስ ከጫፍ ደርሳለች፤ ነገ በማለዳ ይጠብቋት
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ ጋዜጣዎ ሳምንቷን ጠብቃ ከእጅዎ ልትደርስ ከጫፍ ደርሳለች፤ ነገ በማለዳ ይጠብቋት

አጋራ
አጋራ

ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው የመጀመሪያዋ ባለቀለም ጋዜጣዎ ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስ እና አነጋጋሪ ዘገባዎችን እንደዚሁም ያልተሰሙ ቃለ-ምልልሶችን ይዛ ነገ በማለዳው ከእጅዎ ትገባለች፡፡
ሀትሪክ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ የመቐለ 70 እንደርታው ተደናቂ ተጨዋች ዮናስ ገረመው /አላባ/ በክለባቸው የሊጉ የውድድር ተሳትፎ ዙሪያና ከቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ረቡዕ ስለሚያደርጉት ጨዋታ ይናገራል፤ ምን ብሎ ይሆን ምላሹን ነገ ታገኙታላችሁ፤ ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከምታስነብቦት ውስጥ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር ተሳትፎ ላይ የሞሮኮውን ክለብ በመፋለም በአጠቃላይ ውጤት 5-0 ስለተሸነፈው የጅማ አባጅፋር ክለብ ረዳት አሰልጣኙ የሱፍ ዓሊ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሚዲያ ደረጃ ሰጥተዋል ስለተባለው የመልሱን ጨዋታ ውጤት እንቀለብሰዋለን ባለው ጉዳይ ላይ ሀትሪክ አነጋግራው አሰልጣኙ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በሌላው በአንባቢዎቿ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈችበት በመጣችው The Big Interview አምዷ ላይም በነገው እትም የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ የሐዋሳ ከነማ የሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች የነበረውና በአሁን ሰዓት ለቅ/ጊዮርጊስ ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘውን የአምናው የፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች አቡድልከሪም መሐመድን ይዛ ቀርባ ተጨዋቹ ምርጥ ቃለ ምልልስን ሰጥቷል፡፡ የሀትሪክ የነገ እትም እንዳያመልጦ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ድል ከቀናቸው ክለቦች መካከል ወሳኝ የነበሩትን ጨዋታዎች በመዳሰስና ሊወዷቸው የሚችሉ ቃለ ምልልሶችንም ጣፋጭ በሆነ መልኩ በማቅረብ ለእናንተ ልናስኮመኩሞት ዝግጁ ነን፤ ሌሎች መረጃዎችም ሀትሪክ አላት፤ ነገ ማለዳ ይጠብቁን፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...