የ11ኛው ሳምት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ረቡዕ እና ሐሙስ የተከናወኑ ሲሆን እኛ ደግሞ የተጫዋቾችን እንቅስቃሴ መሰረት አድርገን የተመለከትናቸውን ዓበይት የሳምንቱ ጉዳዮች አንሰተንላቹሀል።
ሳዲቅ ሴቾ
ወልቂጤ ከተማ ከትላንት በስታያ በሊጉ ግርጌ የሚገኘው ሀድያ ሆሳዕና በሜዳው እና ደጋፊው ፊት ሲያሸንፍ። ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ያለው ሳዲቅ ሴቾ ባስቆጠራት ቡድኑ ሁለተኛ ተከታታይ ድል እንዲያስመዘግብ የሱ ግብ አስተዋፅኦ ነበረው። ተጫዋቹ ባለፈው ሳምንትም ቡድኑ ድሬዳዋን ሲያሸንፍ ግብ በማስቆጠር ወልቂጤ ከተማ ማግኘት ከነበረበት 6 ነጥብ 6ቱን እንዲያሳካ የነበረው አስተዋፅኦም ከፍተኛ ነው።

አለልኝ አዘነ
ሀዋሳ ከተማ በሜዳው በወላይታ ድቻን ተፈትኖ ባሸነፈበት ጨዋታ። አለልኝ አዘነ በ93ኛው ደቂቃ ለሀዋሳ ከተማ ግብ አስቆጥሮ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ከማስጨበጡም በተጨማሪ። የድቻ ተከታታይ አሸናፊነት እንዲገታም አድርጓል።

አዲስ ግደይ
በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ፍክክር ውስጥ ከሚገኙት ተጫዋቾች መሀከል አንዱ አዲስ ግደይ በዚህ ሳምን ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ትላንት በተደረገው ጨዋታ ሁለት ግቦችን ከማስቆጠሩም በላይ የግብ አጋጣሚዎች እንዲፈጠሩ በግሉ እንቅስቃሴ የተቃራኒ ቡድንን ሲረብሽ ተስተውሏል። በ7 ግቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሙሄዲን ሙሳ
ወጣቱ አጥቂ ሙሄዲን ሙሳ ድሬዳዋ ከተማ ሰበታን ባሸነፈበት ጨዋታ የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ ተጫዋች ሲሆን። ተከታታይ ሁለተኛ ግቡንም ማስቆጠሮ ችሏል። ድንቅ አቋሙን በየጨዋታዎች እያሳየ የሚገኘው ተጫዋቹ። በሊጉ 3 ግብ ያስቆጠረ ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊስን መረብ የደፈረ ብቸኛው ወጣት አጥቂ ነው።

ኦኪኪ አፎላቢ
በ9ኛ ሳምንት ግብ በማስቆጠር ሀ ብሎ የጀመረው ኦኪኪ አፎላቢ በ11ኛው ሳምንትም የፍፁም ቅጣት ምት ቢያመክንም። ግብ ከማስቆጠር ወደ ኋላ ሳይል መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን እንዲያጠናክር ያበረከተ ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ነው።

ሙጂብ ቃሲም
የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሙጂብ መጀመሪያ ከነበረው የግብ አምራችነቱ ወጣ ገባ አቋም እያሳየ ይገኛል ከጅማ አባ ጅፋር ጋር በነበረው ጨዋታም ግብ ሳያስቆጥር ወጥቷል።

አስተያየት ይስጡ