ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

*……የሊግ ካምፓኒ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ እንግዳችን ናቸው… ስለ ኮቪድ 19፣ ስለ ድሬዳዋ ሙቀትና ስታዲየሙ እንዲሁም በኮቪድ ምርመራ 21 ተጨዋቾች ተያዙ ተብሎ አይ 3 ብቻ ናቸው ያለባቸው የሚለው ተጻራሪ ውጤት ዋነኛ ችግሩ የመመርመሪያ መሳርያው ወይስ የእውቀት ችግር?…. የጨዋታ ኮሚሽነሮች ፕሮቶኮል ወጥ ያልሆነው ለምን ይሆን? በሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ይስሃቅ በላይና አቶ ክፍሌ በርካታ ቁምነገሮች ላይ ተከራክረዋል…….

*… የሽገር ደርቢ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ሊካሄድ ወደ 50 ሰአት አካባቢ ቀርቷል…..ከከተማው የራቀው የሽገር ደርቢ እሁድ ምሽት 1 ሰአት ከመካሄዱ በፊት የኢትዮዽያ ቡናው ሬድዋን ናስር “የመጀመርያ ዙር ድል ይደገማል አቡበከርም ሃትሪክ ይሰራል” ሲል የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሙላለም መስፍን
/ዴኮ/ በበኩሉ “ኢትዮዽያ ቡና የመጀመርያ ዙር ድሉን ፈጽሞ አይደግምም” ሲሉ የየበኩላቸውን ፉከራ አሰምተዋል…

*…የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ አሽናፊ ቀን ሊወጣለት ነው… ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ አሽናፊ ለሆነ ክለብ 150ሺ እና 250ሺ ብር ይሰጥ እንዳልነበር አሁን ሻምፒዮን ለሆነው ክለብ የብሮድካስቲንግና የሜሪት ክፍያን ሳይጨምር 1 ሚሊዮን ብር ለሽልማት ተዘጋጅቷል ተብሏል የሊግ ካምፓኒው አመራሮች የሰጡትን መግለጫ ይዘናል…

ከውጪ ዘገባዎቻችን:-

*…. ለዩሮፓ ሊግ ወሳኝ የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ስለደረሱት አርሰናልና ማን.ዩናይትድ ስለኮከቦቻቸው ላካዜትና ካቫኒ ስኬት የምንላችሁም አለ…

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

https://www.Hatricksport.net

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team