ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን የስፖርት ዞን የበጎ ሰው አሸናፊው ሳሙኤል ዮሀንስ እንግዳችን ነው…50 ህጻናትን እንደ ቤተሰብ እንደ ዋናው ጉዳይ አድርጎ እየረዳ ያለ ልባም ተጨዋችም ነው ..ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ የነበረው ተሸላሚው አለማዊ ጉጉት ትኩረቱን እንደማይወስድበት የገለጸው “ጓደኞቼ ቤትና መኪና ገዝተዋል ይሄ ግን አያዝናናኝም የኔ ደስታ ብዙዎችን ረድቶ ማቆም መቻል ነው” በማለት ነው።

*….በኬንያ እየተካሄደ ባለው የሴካፋ ሻምፒዮና እየደመቀ ያለውና በግብ የተንበሸበሸ ቡድን የገነባው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው” የወንዶች ቡድንን የማሰልጠን ህልምም ፍላጎትም የለኝም ማሰልጠን ሳቆም ጥሩ ገበሬ መሆን ነው ምኞቴ”ሲል በተለይ ከሀትሪኩ ይስሃቅ በላይ ጋር በነበረው ቆይታ ላይ ገልጿል።

*… ከመሸሻ ወልዴ ጋር ቆይታ የነበረው የኢትዮጵያ ቡናው ወንድሜነህ ደረጄ “በኮንፌዴሬሽን ካፑ ምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባትና የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት አቅደናል” ሲል የወላይታ ድቻው ግብ ጠባቂ ፅዮን መርዕድ በበኩሉ “የዋሊያዎቹን ስብስብ ዳግም እንደምቀላቀልና ወላይታ ድቻን ለጥሩ ውጤት እንደማበቃው ርግጠኛ ነኝ” ሲል ያለውን ተስፋ ተናግሯል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*…. ” ከ12 አመታት በኋላ ወደ ኦልድትራፎርድ የተመለሰው ሪከርድ ሰባሪው ክርስቲያኖ ሮናልዶ “ማን.ዩናይትድ በድጋሚ ታላላቅ ክብሮችን እንዲያሳካ ማገዝ እፈልጋለሁ” ሲል ተናግሯል…የማዴይራው ልኡልን ቃለ ምልልስ ይዘናል….

*…የሊቨርፑሉ ጆርዳን ሄንደርሰን “እያንዳንዱ ቀን ለኔ አዲስ ነው..ሁልጊዜም በለውጥ ሂደት ውስጥ ነኝ”ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ሊቨርፑል የተከላካዩ ናትናኤል ፊሊፕስ ውልንም አድሷል…ሁለቱን የሚመለከት ዘገባንም ይዘናል።

*….. ቸልሲ የአትሌቲኮ ማድሪዱን ሳኡል ንጉዌዝን አስፈርሟል…ስታምፎርድ ብሪጅ ስለደረሰው የአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ተመራጭ የሚገልጽ ዘገባንም አካተናል።

*…በሶስት ጨዋታ ያለምንም ነጥብ በ8 የግብ ዕዳ በፕሪሚየር ሊጉ 20ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል የኋላው መስመሩን ለማጠናከር ከቦሎኛ ስላስፈረመው አዲሱ ጃፓናዊ መድፈኛ ታኪዬሮ ቶሚያሱ የምንላችሁም ይኖረናል…

*…..በአለማችን እግርኳስ አስሩ ከፍተኛ ሳምንታዊ ደመወዝተኛ እነማን ናቸው? ከሊዮኔል ሜሲ እስከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ከአንቷን ግሪዝማን እስከ ኔይማር ጁኒየር ፣ ከኬሊያን ምባፔ እስከ ኬቨን ደብሮይነ ድረስ ተካተዋል…

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team