ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በገበያ ላይ
ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋ እና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ከእጅዎ ልትደርስ ስራዋን አጠናቃለች፤ ለመሆኑ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? በጉጉት ለማንበብ እንዲችሉ ከወዲሁ እንነግሮታለን፡፡
ሀትሪክ ነገ ገበያ ላይ ስትውል ለእናንተ ውድ አንባቢዎቻችን ከምታስነብቦት መረጃዎች መካከል ፈረንሳዊው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የሰጡት አነጋጋሪ የሆነ /exclusive/ ቃለ-ምልልስ ይገኝበታል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕን ዋንጫ ካነሳው የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ጎሜዝ ጋር ባደረገው ቆይታም ስለ ኢትዮጵያ ቡና እቅዳቸው፣ ስለ ስልጠና ህይወታቸው፣ ለተጨዋቾች ንቀት አለባቸው ስለመባሉ፣ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች አማኑኤል ዩሃንስና ክለቡን በክብር ስለለቀቀው መስዑድ መሐመድ፣ ስለ ጎበኟቸው ታሪካዊ ስፍራዎች እና ሌሎችም ያልሰሙ ቃለ-ምልልሶችን አድርገዋል፤ ሀትሪክን ነገ ይጠብቋት፤ እንዳታመልጦት፤ ሀትሪክ ከዚህ መረጃዋ በተጨማሪም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ኃላፊነቱ ከተሰጣቸው ኮሎኔል አወል አብዱራሂም ጋርም በህትመት ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጡት /exclusive/ ቃለ-ምልልስም ይገኝበታል፤ ሌሎች መረጃዎችም አላት፤ ነገ ሀትሪክን ያንብቧት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በባህር ማዶ የነገው ዘገባዋ በባርሴሎና የበላይነት ስለተጠናቀቀው ኤል ክላሲኮ ጨዋታም የሚወዱትን መረጃ ያቀረበችሎት ሲሆን የታላላቆቹ የአውሮፓ ሀገራትም የሊግ ውድድሮች የዳሰሰችውን ታቀርብሎታለች፡፡
ሀትሪክ የእርሶ ናት፤ መልካም ንባብ ይሁንሎት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው ፊት ለፊ ገፅ ይህንን ይመስላል
አስተያየት ይስጡ