መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በገበያ ላይ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የማክሰኞ እትሟ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በገበያ ላይ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የማክሰኞ እትሟ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በገበያ ላይ
ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የማክሰኞ እትሟ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ነገ ለእናንተ ውድ አንባቢዎቻችን ልታስነብቦት ከተዘጋጀችበት ዘገባዎች መካከል ከወልዲያ ከተማ ጋር በተያያዘ ቡድኑ ከፋሲል ከተማ ጋር በተጫወተበት እለት በተነሳው ረብሻ ጉዳትን ካስተናገደው የቡድኑ አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ጋር ቃለ-ምልልስን ያደረግን ሲሆን ከእዚያ ውጪ በሄኒይከን ስፖንሰር አድራጊነት ወደ አገራችን መጥቶ ጥሩና ጣፋጭ ቆይታን ለሁለተ ቀናት ስላደረገው ብራዚላዊው የእግር ኳሱ ዓለም ድንቅ ተጨዋች ሮናልዲኒኦ ጎቾ አሲስ ሞራ የተሰራ ዘገባ ተሰናድቶላችኋል፤ ከሀገር ውስጥ ሌሎቹ ይዘንላችሁ የቀረብነው ዘገባ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር ተሳትፎ ወደምድብ ድልድል ለመግባት በሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ አገራችንን ወክለው ስለሚሳተፉት የቅዱስ ጊዮርጊስና የወላይታ ድቻ ክለቦች ነገ ከካራ ብራዛቪልና ያንግ አፍሪካ ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ ዙሪያ ሰፋ ያለ ዘገባና የተጨዋቾች አስተያየት ይዘንሎት ቀርበናል፤ ሀትሪክ ስፖርት ሌላው በየሳምንቱ ከምታስነብቦት ውስጥ የቀድሞ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዷ ነገ ይዛው የምትወጣውና ታሪኩን የምታስኮመኩሞት ተጨዋች በአማካይ ስፍራ ላይ ጥሩ ብቃቱን አሳይቶ በመጫወት ያሳለፈውን የቀድሞ የኦሜድላና የኪቤአድ ተጨዋች የነበረውን ነገደ ደስታን ሲሆን እሱም ላቀረብንለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቶናል፤ ሀትሪክ ነገ አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትም በባህር ማዶ ዘገባዋም ልታስነብቦት የተዘጋጀችው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ሻምፒዮናነቱን ስላረጋገጠው ማንቸስተር ሲቲም የምናስነብቦት ሰፋ ያለ ዘገባም አለ፤ ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.comድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...