መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጥር 9 ቀን 2009 ዓ/ም እትሟ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጥር 9 ቀን 2009 ዓ/ም እትሟ

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው ጥር 9 ቀን 2009 ዓ/ም እትሟ በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የስፖርት ዘገባዎች ላይ እናንተ ልትወዷቸው የምትችሉትን ምርጥ ዘገባዎች ይዛላችሁ ትቀርባለች፤ ከሀገር ውስጥ ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ተደናቂ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስቻለው ታመነ ጋር በፕሪምየር ሊጉ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ቡድናቸው ከሐዋሳ ከተማ ጋር ሲጫወት በቅንድቡ ላይ በክርን ከተመታ በኋላ በደረሰበት ጉዳትና አቻ ስለተለያዩበት ጨዋታ እንደዚሁም ደግሞ በቡድናቸው ወቅታዊ አቋም ዙሪያ ለምሳሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን መሪነት ስለጨበጠበትና እየተከተለው ስላለው አጨዋወት የሚለው አለ፤ ሌላው ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናው ስኬታማ ተጨዋች አስቻለው ግርማ ቡድናቸው ወደ ጅማ በመጓዝ ድል ስላደረገበት ጨዋታ እና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያ ለምሳሌ ሰርቢያዊው አሰልጣኙ ከኃላፊነት ከተነሱ በኋላ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ ስለሆኑበት እንደዚሁም ደግሞ የኤሌክትሪክ ምርጡ አማካይ በኃይሉ ተሻገር /አኪራ/ ቡድናቸው ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የመጀመሪያ የሊጉን ድላቸው ስላስመዘገቡበትና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተንተርሰን ጠይቀናቸው ምላሻቸውን ሊሰጡን ችለዋል፡፡ ሌላው የሀገር ውስጥ ዘገባ ቅዳሜ ዕለት በይፋ ስለተመረቀውና በአይነቱ ምርጥ ስለሆነው የወልዲያ ዘመናዊ ስታዲየም ሀትሪክ ሰፋ ያለ ዘገባን ይዛላችሁ መጥታለች ተከታተሏት፤ ከባህር ማዶ ዘገባዎች ደግሞ ምርጡን የእግር ኳስ ዘመን  ስላሳለፈው ምርጡ ተጨዋች ክርስቲያን ሮናልዶ ሰፊ ዘገባን ሀትሪክ ይዛላችሁ ቀርባለች፤ ቼልሲን አስመልክቶም  በእርግጥ የዲያጎ ኮስታ እና የአሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን የእርስ በእርስ ግንኝነት አስመልክቶ የሁለቱ ፍቅር ተቋጭቷል በሚል የቀረበ ሰፊ ዘገባ በሀትሪክ ላይ ተዳስሷል፤ ስለ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ደግሞ በማንቸስተር ዩናይትድ ማሊያ ማንነቴን በማስመስከሬ ስኮራ እኖራለሁ” በሚል እርሱ ሊቨርፑል  ላይ የአቻነቷን ግብ ካስቆጠረ እና ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላም የሰጠውን አስተያየት ሀትሪክ በዘገባዎቿ የዳሰሰችው ሲሆን የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቪንገርም በእኔና በሳንቼዝ መካከል ምንም አይነት ግጭት የለም በሚልም የሰጡት አስተያየት አለ፤ ሀትሪክ ከእነዚህ ውጪም በመዝናኛ አምዷ ጣፋጭ እና ልትደሰቱባቸው የምትችሉትን ሌሎች ዘገባዎችም ይዛላችሁ ነገ ጠዋት ብቅ ትላለች፤ ሀትሪክ የእርሶ ናት ነገ እንዳታምልጦት፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...