ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣን በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ዘወትር ቅዳሜ በገበያ ላይ ያገኟቷል።

ሀትሪክ ስፖርት በገበያ ላይ
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ምስል ይህን ይመስላል
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣን በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ዘወትር ቅዳሜ በገበያ ላይ ያገኟቷል።
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት ዘ ቢግ ኢንተርቪው አምዷ በክረምቱ ወራት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከአዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ከነሃን ማርክነህ ከጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ ከሆነው ይስሃቅ በላይ ጋር ባሳለፈው የኳስ ህይወት ዙሪያው እና ስለ አዲስ ቡድኑ ጥያቄዎች ቀርቦለት ምላሾቹን ሰጥቷል።
ሀትሪክ ከዛ ውጪም በቅርቡ ታዋቂው አርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት ምሽት ከፍተኛ ንብረቱ የወደመበት ሻለቃ ሀይሌ ገብረ ስላሴ ስለ ንብረቱ ዉድመት የሚላችሁ ይኖራል።
ሀትሪክ ከእዛ ውጪም ፋሲል ከነማን በዝውውር መስኮቱ ከወልቂጤ ከተማ በመምጣት የተቀላቀለው ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔም የሚላችሁ ነገር ይኖራል። ምን ብለው ይሆን? ሀትሪክ ሌሎች አጫጭር መረጃም አላት።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ሊጎቻቸው ሊጠናቀቁ ከጫፍ ስለደረሱት የአውሮፓ ውድድሮችም መረጃዋን ታቀርብሎታለች ያንብቧት።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team