ሀትሪክ ስፖርት በገበያ ላይ፤ ነገ ይጠብቋት ሀትሪክ ስፖርት በተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ታጅባ ለእርስዎ ውድና የተከበሩ አንባቢዋ ነገ በገበያ ላይ ትውላለች።

ሀትሪክ ስፖርት በገበያ ላይ፤ ነገ ይጠብቋት
ሀትሪክ ስፖርት በተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ታጅባ ለእርስዎ ውድና የተከበሩ አንባቢዋ ነገ በገበያ ላይ ትውላለች።
ሀትሪክ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛለች?
በሀገር ውስጥ እትሟ በኮሮና ቫይረስ የተቋረጠውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አስመልክቶና ስለ ቫይረሱ መስፋፋት የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች የሆነውን ፈቱዲን ጀማልን አናግረነዋል። ተጨዋቹ ምን ብሎ ይሆን? አጠቃላይ ምላሹን ከጋዜጣው ያገኙታል።
ሀትሪክ ስፖርት ሌላ የምታቀርብሎት መረጃ THE BIG INTERVIEW በሚለው ተወዳጅ አምድ በቀድሞ ጊዜ ለመብራት ሀይል ለመከላከያ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተጫወተው ጠንካራው ተጨዋች መስፍን አሰፋ ቻይና ከሚኖርበት እንግሊዝ ሀገር በመምጣት በተጨዋችነት ዘመኑ ስላሳለፋቸው ጊዜያት ስለ እንግሊዝ አኗኗሩ ስለ ተጫወተባቸው ክለቦች ስለ ትዳር ህይወቱ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ስለተመለከታቸው ጨዋታዎች እና በአሁን ሰዓት ለዓለም ስጋት ስለ ሆነው ኮሮና ቫይረስና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርቦለት ለሁሉም ምላሽን ሰጥቷል።

ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ስለ ኮሮና ቫይረስና ጊዜውን እያሳለፉ ስላለበት መንገድ እንደዚሁም ስለ ቦሩሲያ ዶርትመንዱ ወርቃማ ተጨዋች ዴጃን ሳንቾ እንደዚሁም በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ስለነበረው የአርሰናሉ አለቃ ሚካሄል አርቴታ እና ሌላም የሚወዷቸው መረጃዎች አሏት።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪም ከፍተኛ መሻሻልን ባሳየውና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋም hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
ሀትሪክ አታምልጦት
የሀትሪክ የፊት ለፊት ገጿም ይህንን ይመስላል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team