ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትም
ባለቀለሟ ጋዜጣዎ ሀትሪክ ስፖርት ተወዳጅ እና ተናፋቂ ጋዜጣ ስለመሆኗ ብዙዎች ምስክርነትን ሰጥተዋታል፤
በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የተለያዩ ክለብ ተጨዋቾችን እና አሰልጣኞችን የህይወት ታሪክ እና ከጨዋታዎች በኋላም ስለሚሰጡት አስተያየት በየጊዜው እንግዳዋ አድርጋ በማቅረብ ከእናንተ ጋር የምታስተዋውቆት እና ሌሎች የዜና ዘገባዎቿንም የምታስነብቦት ሀትሪክ ስፖርት ነገም በገበያ ላይ ስትውል የሚወዱትን መረጃዎች ይዛሎት ትቀርባለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ለመሆኑ ነገ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
THE BIG INTERVIEW በሚለው እና ብዙ ተከታታይ ባላት አምዷ ነገ የምታቀርብሎት ተጨዋች የቅዱስ ጊዮርጊሱን አጥቂ አቤል ያለውን ነው፤ አቤል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች ቀርቦለት ምላሽን ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት ሌላ ይዛቸው ከምትቀርባቸው ዘገባዎች መካከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ባዘጋጀው የሁለት ቀናት ውይይት ዙሪያ ሲሆን ሌላው ኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳር ከነማን በሰፊ ግብ ባሸነፈበት ጨዋታ ዙሪያ ሁለት የድል ጎሎችን ካስቆጠረው አቡበከር ናስር ጋር ስለ ቡድናቸው ድል፤ ስላስቆጠረው ተደናቂ ግብ እና ከሜዳም በቀይ ካርድ ስለመውጣቱ ጠይቀነው ምላሽን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎችም ወደ ወሳኝ ምሕራፍ ላይ እየተሸጋገረ ስለመጣው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊጉ ውድድር ዙሪያና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጣሊያን ሴሪ አ ከጁቬንቱስ ጋር ጣፋጭ ድል ስለመጎናፀፉና በእግር ኳስ ህይወቱም በተለያዩ ሀገራት ውድድሮች ላይ አዳዲስ ሪከርዶችንም እያስመዘገበ ስለመሆኑ የምታነቡት መረጃ ሀትሪክ ይኖራታል፡፡
ሀትሪክ የእናንተው ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ