ሀትሪክ ስፖርት በማክሰኞ እትሟ
ባለቀለሟ፣ ሳምንታዊዋ እና ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣዎ ነገም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛ ለመውጣት ተዘጋጅታለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ የነገ ዘገባዋ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማሪያም ጋር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያና ከስልጠና ህይወቱ ጋር በተያያዘ የሚወዱት ዘገባ አላት፤ ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባ የሌሴቶ አቻውን ባህር ዳር ላይ ነገ ስለሚፋለም ብሄራዊ ቡድናችን ዘገባ እና ስለጨዋታው ከተጨዋች አህመድ ረሺድ ሺሪላ ጋር ቆይታ አላት፤ ሌላው ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማውን ስላኖረው የባህር ዳር ከተማው ተከላካይ ወንድሜነህ ደረጄም ጋር በተያያዘ ለተጨዋቹ ባነሳንለት ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቶናል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ የነገ ዘገባዋም የአውሮፓ ኮከብ ተጨዋችነትን ክብር ስላገኘው የሊቨርፑሉ ቫንዳይክ እንደዚሁም ደግሞ እሁድ ዕለት ስለተደረገው የአርሰናልና የቶተንሃም ጨዋታ ዙሪያና በሌሎቹም የሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ የምትሰጦት መረጃ ይገኛልና የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ