መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ሳምንታዊዋ ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ከጥሩ ጥሩ ዘገባዎቿ ጋር ለእናንተ ውድ አንባቢዎች ልትቀርብ ከጫፍ ደርሳለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ሳምንታዊዋ ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ከጥሩ ጥሩ ዘገባዎቿ ጋር ለእናንተ ውድ አንባቢዎች ልትቀርብ ከጫፍ ደርሳለች፡፡

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት፣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ
ሳምንታዊዋ ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ከጥሩ ጥሩ ዘገባዎቿ ጋር ለእናንተ ውድ አንባቢዎች ልትቀርብ ከጫፍ ደርሳለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
ሀትሪክ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት The Big Interview አምዷ
በጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡናውን ዋና አሰልጣኝ ፈረንሳዊውን ዲዲዬ ጎሜዝን በህትመት ሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ አድርጋ ያቀረበችው ሀትሪክ አሁን ደግሞ በሌላ አዲስ ታሪክ ለኢትዮጵያ ፉትቦል እንግዳ የሆኑትን እንግሊዛዊውን የቅ/ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ስቲዋርት ጆንን በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ በማድረግ ለተከበሩ አንባቢዎቿ ይዛ ቀርባለች፡፡
አሰልጣኙ ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለስልጠና ህይወታቸው፣ ስለ ግል ህይወታቸው፣ ስለሚያደንቁት አሰልጣኝና በተለይ ስለ አዲሱ ክለባቸው ቅ/ጊዮርጊስ እና አብረውት ለማሳካት ስለሚያስቡት ዕቅዳቸው በስፋት ምላሽ ሰጥተዋል፤ ቃለ-ምልልሱ የአሰልጣኙን ማንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና የነገዋ ሀትሪክ እንዳታመልጥዎ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሀትሪክ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ ጅማ አባ ጅፋር ከግብፁ አልአህሊ ጋር የፊታችን ዐርብ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ስለሚያደርገው ጨዋታ ከቡድኑ ተጨዋች ሀወት ገብረሚካሄል ጋር ያደረግነው ቃለ-ምልልስ ያለ ሲሆን ከዛ ውጪም በሊጉ የ6ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ከሐዋሳ ከነማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ግጥሚያው ስለመቋረጡ እና ትናንት ስለመቀጠሉ መረጃ አለን፤ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ባህርዳር ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን ባሸነፈበት ጨዋታ ዙሪያና በክለቡ ዙሪያ የባህር ዳሩ ተጨዋች ግርማ ዲሳሳ የሚለውም አለ፤ ሀትሪክ ሌሎችም መረጃዎች አሏት፤ ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል ማንቸስተር ዩናይትድን በመርታት መሪነቱን ባስጠበቀበት ጨዋታ ዙሪያና ሌሎች ጣፋጭ መረጃዎችን ሀትሪክ ይዛሎት ቀርባለች፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...