መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርትን ያንብቡ፤ ፈፅሞ አታምልጦት በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የሚወዷቸውን ዘገባዎች ይዛሎት ትቀርባለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ ስፖርትን ያንብቡ፤ ፈፅሞ አታምልጦት በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የሚወዷቸውን ዘገባዎች ይዛሎት ትቀርባለች፡፡

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን፤
ከሀገር ውስጥ The big Interview በሚለው አምድ ይዘንሎት የቀረብነው ተጨዋች ላለፉት 15 ዓመታት ለሐዋሳ ከነማ፣ ለቅ/ጊዮርጊስና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተጫወተውን እና በተደጋጋሚ ጊዜም የኮከብ ግብ አግቢ ተብሎ የተሸለመውን ታዋቂውን አዳነ ግርማን ሲሆን ከተጨዋቹ ጋር በኳስ ሕይወቱና በሌሎችም ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረነው ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ የፊታችን እሁድ በቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ስለሚደረገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ከቡድኑ ተጨዋቾች ውስጥ በደርቢው ጨዋታ የሁለት ጊዜ የመጫወት ዕድል ካገኘው የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር ጋርና ለመጀመሪያ ጊዜ በደርቢው ጨዋታ ሊሳተፍ ከተዘጋጀው የቅ/ጊዮርጊሱ ሄኖክ አዱኛ ጋር ቆይታ አድርገን ተጨዋቾቹ ምላሽ ሰጥተዋል፤ ሀትሪክ ሌሎችም መረጃዎች አሏት፤ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ከባህር ማዶ ዘገባዎቿ መካከል ደግሞ በነገው አትሟ የምታስነብቦት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል የሊጉን መሪነት እያጠናከረ ስለተጓዘበት አካሄድ እና የቡድኑ አጥቂ መሐመድ ሳላህ ችሎታም ሳያቋርጥ እየተሻሻለ ስላለበት ሁኔታ፣ የአርሰናሉ አጥቂም አቡሚያንግ ቡድኑን ወደ አሸናፊነት እያስጓዘ እና ራሱንም ወደ ኮከብ ግብ አግቢነት ከፍ እያደረገ ስላለበት አካሄድና የማንቸስተሩ አዲስ አሰልጣኝ ሶልሻየር ክለቡን ለመጀመሪያ ጊዜ በመራበት የሊጉ ጨዋታ ድንቅ አጀማመር ስለማድረጉ ዘገባዎች ቀርቦሎታል፤ ሀትሪክ ሌሎችም የሚወዷቸው መረጃዎች አሏት፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው እትም የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...