ሀትሪክ ስፖርትን ነገ ይጠብቋት ምንን ይዛ ወጥታ ታስነብቦት ይሆን።

ሀትሪክ ስፖርትን ነገ ይጠብቋት
ምንን ይዛ ወጥታ ታስነብቦት ይሆን።
በሀገር ውስጥ ዘገባ “ለኢትዮጵያ ቡና ያስቆጠርኩት ጎል በሊጉ የመጀመሪያዬ ስለሆነች ለየት ያለ ደስታ ተሰምቶኛል” ይላል የቡናው
ሚኪያስ መኮንን። ሌላስ ምን ምን አስተያየቶችን ለጋዜጣው ተናግሮ ይሆን?
ከእሱ ሌላም THE BIG INTERVIW በሚለው አምድ “ኢትዮጵያዊነት ሰፍቶ ዘረኝነት ከምድሪቱ ተወግዶ ማየት እመኛለው”
“መቐለ 70 እንደርታን ጠንካራ ያደረጉት ኳስን በእውቀት የሚደግፉት ደጋፊዎቻችን ናቸው” የሚሉና
“2ኛ ዙር ላይ ማየት የማልፈልገው የዳኞችን የስህተት ውሳኔ ነው….” በማለት የመቀለ 70 እንደርታው
ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ ም ይናገራል።
ከዛ ውጪም የሲዳማ ቡናው ስራ አስኪያጅና የሊግ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንግስቱ ሳሳሞም
“እናንተ ጋዜጠኞች ለምትፈልጉትና ለከፈላችሁ ታወራላችሁ፤ ለማትወዱትና ላልከፈላችሁ አታወሩም”
“እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ከራሱ አንፃር የሚጠቅመውን እንጂ ሰው የሚያመውን አይደለም የምትሰሩት” ብሏል።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባም የአርሰናሉ ላካዜት የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታቸውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጨዋታው ፈታኝ ነው ስላለበት በማንቸስተር ዩናይትድ አሸናፊነት ስለተጠናቀቀው የማንቹኒያን ደርቢ ጨዋታና ነገና ረቡዕ ስለሚደረጉት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች የሚወዱትን ዘገባ አቅርበንሎታል።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪም ከፍተኛ መሻሻልን ባሳየውና በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋም hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
ሀትሪክ አታምልጦት
የሀትሪክ የፊት ለፊት ገጿም ይህንን ይመስላል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team